ጠላታችንም ዕቅድ አለው

ጠላታችንም ዕቅድ አለው

ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፤ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል። – 1 ኛጴጥ 5፡8

እግዚያብሔር ለህይወታችሁ ዓላማ እንዳለው ሁሉ ሰይጣንም ዓላማ አለው፡፡ ስለዚህም መፅሃፍ ቅዱስ ሁሌም ሚዛናዊ (ራሳችንን የምንገዛ) እንድንሆን ፣ ሁል ጊዜም ነቁ እንድንሆን ነግረናል፡፡

ራስን መግዛት ማለት ስነምግባራዊ መሆን ማለት ነው፤ ንቁ ማለት ደግሞ ጥንቁቃን ሁኑ ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ ሁልጊዜም ቢሆን በጣም በጥንቃቄ በተሞላ መልኩ ልንኖር ይገባናል ማለት ነው ምክንያቱም ጉዳዬ በጣም ወሳኝ ነው፡፡

ጠላታችንን ለመፋለም እጅግ በጣም ንቁና ቆራጦች መሆን መቻል አለብን፡፡ እግዚያብሔር በህይወትህ ውስጥ ጠላት በየትኛው ቦታ ጥቃት እየፈፀመብህ እንዳለ ሲያሳይኽ፤ ዝም ብለኽ እንድትቀመጥና ምንም እንዳታደርግ አይደለም፡፡ ነገርግን በጣም በአንክሮ በሰይጣን ላይ ጥቃት በመፈፀም እንድትዋጋው ነው፡፡

የእግዚያብሔር ለእኛ ያለው ዓላማ በክርስቶስ አሸናፊዎች እንድንሆን ነው፡፡ ለጠላታችን ዓላማ ባሪያ መሆን የለብንም። አሁን መስራት ያለብህን ለመስራት ውሳኔው በእጅህ ነው፡፡ ከእግዚያብሔር ጋር በቁም ነገር ተገናኝ ፣ የመንፈስ ቅዱስን ምላሽም አድምጥ ፣ ጠላትህንም ለመከላከል በተጠንቀቅ ቁም፡፡ እግዚያብሔር በህይወትህ ያለውን ዓላማ ለመገናኘት ዛሬ እግዚያብሔርን ለመከተል ወስን፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ የጠላቴን ዓላማ ሳይሆን የአንተን ዓላማ መርጫለሁ፤ ጠላቴ በየትኛው በኩል እያጠቃኝ እንደሆነ አሳየኝ እንዳሸንፈውም እርዳኝ፡፡ ጠላቴ የሚያጠቃኝን ቦታ አሳየኝና እሱን ወደማሸነፍ ይምራኝ ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon