እውነተኛ እምነት

እውነተኛ እምነት

«የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው» (1ኛጢሞ.1።5)።

በእምነታችን ወይም በጸሎታችን ህጻን ልንሆን አይገባንም፣ ነገር ግን እኛ መሆን የሚያስፈልገን እንደ ልጆች መሆን ያስፈልገናል። ጌታ ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ውስብስብ እንዲሆን አይፈልግም። እርሱ እውነተኛ ልባችንን ይመረምራል፣ ምክንያቱም እርሱ የልብ አምላክ ነውና። እርሱ በስሜት የሆነ ጸሎት ሳይሆን በእምነት የሆነውን ጸሎት ከእኛ ይፈልጋል። ነገር ግን መንሳዊ ኃይል በማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ላይ ተጸዕኖ ያደርጋልና። እግዚአብሔር የሥርዓት አምላክ ነው እንጂ የመመሪያና የኃይማኖታዊ ሥርዓት አምላክ አይደለም። እርሱ የረጅም ጊዜ ጸሎት እንድንሞክር ሰዓት እንድጨርስ፣ በሥርዓት የተሞላ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሌለበት የረጅም ሰዓትና የተወሰነ ኃይማኖታዊ ገጽታ ያለውን ጸሎት አይፈልግም። ይህ ዓይነት የጸሎት ልምምድ ወደ ወግ አጥባቂ ህጋዊነትና ከእግዚአብሔር ጋር ካላን ህብረት የሚገኘውን ህይወት ይወስድብናል። «ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል» (2ኛቆሮ.3።6)።

እኛ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ስንከተል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት በህይወት የተሞላ ይሆናል። ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉት የጸሎት ሰዓትን ለማሟላት የእጅ ሰዓታችንን አሁንም አሁንም መመልከት አያስፈልገንም። ከእግዚአብሔርን ለመነጋገርና ለመስማት ስንቀርብ እንደ ግዴታናእንደ ሥጋችን ሥራ ስናደርግና ስንቀርብ፣ የአምስት ደቂቃ ጸሎት እንደ ሰዓታት ይቆጠርብናል። ነገር ግን ጸሎታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሞላ ሲሆን ለሰዓታት የምንጸልየው ጸሎት አምስት ደቂቃ የጸለይን አይመስለንም። እኔ የምፈልገው ውስጤ ሙሉ ሆኖ ጥግብ እስኪልና እስኪረካ ድረስ መጸለይና ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ እወዳለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ህብረት የተመቸህና ደስተኛ እንዲያደርግ ለማድረግ ሞክር፣ እርሱ ደግሞ ላንተ የተሰጠህ ደመወዝህ (ዋጋህ) ነው።


ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ እንደልጅነት ለመሆን ጥረት አድርግ አንጂ ህጻን አትሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon