ውጊያውን ቋጭ

ውጊያውን ቋጭ

ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና ፣ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም፡፡ – ገላቲያ 5፡17

እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን ፈቃዱን በተሰካ ሁኔታ ለመፈጸም ቁርጠኝነት ያስፈልገናል፡፡ የቁርጠኝነት አንዱ ትንታኔ ‹‹ አግባብ ባለው የሥልጣን አካል ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ውጊያን መቋጨት›› ማለት ነው፡፡ በአንዳድ ሁኔታዎች ውስጥ አዋጅን ስለማውጅ ከላይ ያስቀመጥኩት ትንታኔ ያበረታታኛል፡፡ ለምሳሌ ድካም ሲሰማኝ አንዳዴም በራሴ ሳዝን ‹‹አይገባም!›› ‹‹ማጉረምረምሽን አቁመሽ ተነሺ›› ብዬ አውጃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይወደኛ ፣ ብርታትን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ማድረግ እችላላሁ፡፡ ገላቲያ 5፡ 17 ሥጋ እና መንፈስ አብረው ዘላቂ እንዳልሆኑ ይናገራል፡፡

አስታውስ የቁርጠኝነት ትንታኔ የውጊያ መቋጪያ ሀሳብን ያሳያል፡፡ ለማንኛውም ነገር መሰጠት የምትፈልጉ ከሆነ አስቀደማችሁ በሥጋ እና በመንፈስ መካከል ያለ እና መቋጫ የሚያስፈልገውን ጦርነት ማቆም ጠቃሚ ነው፡፡

ምናልባት ሁሌም ቁርጠኛ ለመሆን ጥረት አታደርጉ ይሆናል ይሁን እንጂ ተሰፋ አትቁረጡ አሊያ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ ትሆናላችሁ፡፡ ተስፋ የሚያስቆርጥ ፈተና ሲገጥማችሁ በእግዚአብሔር ቃል ላይ መሰረት አድርጋችሁ አዋጅ አውጁ ፤ ለቆራጥነት ራሳችሁን አበረቱ፡፡ በመንፈሳችሁና በሥጋችሁ መካከል ያለውን ውጊያ ፈቃዱን በመከተል ቋጩ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ በሥጋዬ እና በመንፈሴ መካከል ያለው ውጊያ እንዲቋጭ እፈልጋለሁ ፤ እኔ ይህን ማድረግ አልችልም፡፡ ተስፋ እንዳልቆርጥ ፣ እንድበረታ እና ትክክለኛ አዋጅ ማወጅ እንድችል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon