ለሌሎች መድረስ

ለሌሎች መድረስ

ባታንጎራጉርም ፣ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ ፣ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ ፣ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል – ኢሳያስ 58፡10

እግዚብሔር የተጎዱ እና አቅራቦት የሚያሻቸውን መደገፍ ይወዳል ፡፡ እግዚአብሔርን እየቀረብኩ እና ፍቅሬም እያደገ በመጣባቸው አመታት የሰዎች ሕይወት የተሻለ እንዲሆን በየዕለቱ ጥረቴ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር የሚወደው ነገር የኔም ሆነ፡፡

ለሌሎች መድረስ እንዲያው ከንፈር መምጠት ብቻ አይደልመ፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለሚኖሩ ዋናው እና ቀዳሚ መሆን አለበት፡፡ ቁርጠኝነት እና መሰጠት ለሌሎች መዘርጋት ለመርዳት አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለሌሎች መኖር ስትጀመሩ በእናንተ ይጠቀማል፡፡ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል ( ኢሳያስ 58፡ 10 ይመልከቱ)

ከሁኔታዎችህ በላይ ስትዘረጋ እና የክርስቶስን ፍቀር ለሌሎች ስታደርስ ሰላምህና ደስታህ ይጨምራል፡፡ ትግልህም ይደመሰሳል፡፡ በዚህም አስገራሚ እና አርኪ መሆኑ ለውጥን ማምጣት ትለማመዳለህ፡፡

እግዚአብሔር የሚወደውን አንተ የምትወደው ነገር እንዲሆን ማስተካከል እና ቅደመ ሁኔታ ማበጀት ይኖርብህ ይሆን ? እንዴት ሌሎችን መድረስ እንደምትችል እንዲያሳይህ እግዚአብሔር ጠይቅ ፤ የእግዚአብሔርንም ብርሃን እና ፍቅርን ለሌሎች ለሚፈልጉት አድርስ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ ያን ርህራሄ የኔም እንዲሆን እሻለሁ፡፡ ቅድሚያ የምሰጣቸውን ነገሮች እንዳስተካከል እርፋኝ ፤ ለሌሎች መድረስ የምችለበትን መንገድ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon