እግዚአብሔር በሕይወትህ ያለዉን አልዓዛር ሊያስነሳ ይችላል

እግዚአብሔር በሕይወትህ ያለዉን አልዓዛር ሊያስነሳ ይችላል

“…አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳዉ” – ማር 9:24

ስህን በአሳዛኝ ሁኔታ ዉስጥ አግኝተህ እግዚአብሔርን “ለምን” ይኼ ለምን በእኔ ላይ ደረሰ? ብለህ ጠይቀህ ታዉቃለህ?

ለአንድ አፍታ እግዚአብሔር ያንን ጥያቄ መልሷል ብለን እናስብ፣ የእርሱ ማብራሪያ አንዳች ነገር ይቀይራል? የሰቆቃዉ ተጽዕኖ እስካሁን ከአንተ ጋር አለ ህመሙም ልክ እንደበፊቱ ጽኑ ነዉ፡፡ የተማርከዉ ምን ይሆን?

እግዚአብሔርን ያንን ጥያቄ ስንጠይቀዉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ ትወደኛለህ ወይ?” በሐዘኔና በህመሜ ትጠነቀቅልኛለህ? ብቻዬን አትተወኝም አይደል? ትተወኛለህ? እያለን እየጠየቅነዉ እንደሆነ ነዉ እኔ ማስበዉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እኛ አይጠነቀቅም ብለን ስለምንፈራ ይሆን ማብራሪያ የምንጠይቀው?

በምትኩ የግድ እንዲህ ማለት መማር አለብን፤ “ጌታ ሆይ አምናለሁ፡፡ አልረዳዉም ደግሞም ክፉ ነገር የሚከሰትባቸዉን ምክንያቶች ሁሉ መያዝ አልችልም ነገር ግን እንደምትወደኝና ሁል ጊዜም ከእኔ ጋር እንደሆንክ አዉቃለሁ፡፡”

አንድን ነገር ከመላቀቅ ይልቅ ከሱ ለመላቀቅ የምናደርገው የድል ጉዞ የበለጠ እምነት እንደሚጠይቅ አምናለሁ፡፡ እምነትህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፤ በሌላ ጎን ጠንካራ ትሆናለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ዙሪያየ ያለዉ ነገር አእምሮዬን በጥርጣሬ ለመሙላት ቢሞክርም በአንተ አምናለሁ፡፡ ምንም ነገር ቢከሰት ለእኔ ያለህን ፍቅር እስዳስታዉስና እምነቴን በአንቴ ላይ እንዳደርግ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon