መልካሙን ሥራ አድርግ

እኛ ፍጥረቱ ነንና እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን፡፡ ኤፌ. 2 10

ከአመታት በፊት በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር በጣም በቀረበ ወዳጅነት መጋዝ ሲጀምር አካባቢ ለማደርገው እያንዳንዱ ጉዳይ የተለየ ማረጋገጫ እስካገኝ ድረስ እርሱን እጠብቅ ነበር፤፤ መንፈስ በእኔ ውስጥ የሚኖረው እኔ መልካሙን ሥራ ለመሥራት እንድችል እንዲረዳኝ እንደሆነ ጌታ እስኪያስተምረኝ ድረስ እንዲሁ ቀጠልኩ፡፡ በዛው በቅርብ ዓመታት አካባቢ ከእግዚአብሔር ጋር ባለኝ ጉዞዬ አንድ ጊዜ ለአንድ ለተቸገረች ሴት አሥር ዶላር (10 ዶላር) እንዲሰጣት በውስጤ ሞላ ያንን የልቤን ፍላጎትና መነሳሳት ለሶስት ሣምንታት ተሸክሜ ከዚያ በመጨረሻ እንዲህ ብዬ ፀለይኩ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ በእርግጥ አንተ ነህ ለዚህች ሴት ገንዘብ እንድሰጥ የተናከርከኝ; በእርግጥ አንተ ያልከኝ ከሆነ አደርገዋለሁ!›› አሥር ዶላር በወቅቱ ብዙ ስለሆነ ዝም ብዬ ከእግዚአብሔር መመሪያ ሳልቀበል ገንዘብን መበተን የለብኝም አልኩት፡፡ ጌታም በግልፅ ተናገረኝ እንዲህም ብሎ መለሰልኝ፡፡ ጆሲ፡- በእርግጥ የተናገረሽ እኔ እንኳ ባልሆነ አንቺ ለሰው በረከት በሆንሽበት አንቺን ልባርክሽ እጄ አላጠረም! ›› አለኝ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ የመኖር እውነታውና ፍሬ ነገሩ እኛን በመልካምነት ሊገልጠን ነው፡፡ (ገላ 5 22 23 ተመልከት) ስለዚህ ፍላጎታችን መሆን ያለበት ለሰዎች መልካም ለመሆን ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረው እርሱን እንደሚባርክና እርሱ ደግሞ ለሌሎች መልካም በረከት እንዲሆን ነበር፡፡ (ዘፍ 12 2 ተመልከት) በቀላሉ ሌሎችን ለማስደሰትና በረከት ለመሆን የምንችልበትና እግዚአብሔርን የምናገለግልበት ጥግ ለመድረስ ምን ያህል እንደሚያስፈራ አስብ፡፡

ዓለም ብዙ ዓይነት ችግር ያለቸው ሰዎች አሉባት፡፡ አንዳንድ ሁልጊዜ የትም ቦታ የማበረታቻ ቃል ይፈልጋል፡፡ አንዳንዱ ሞግዚት (ሕፃን የምንከባከብላት)፣ አንዳንዱ የመጓጓዣ አገልግሎት፣ አንዳንዱ የገንዘብ እርዳታ ይፈልጋል፡፡ ይህንን መረዳት ያገኘሁት ከእግዚአብሔር ጋር የጥሞና ጊዜ በነበረኝ ጊዜ ሰዎችን የመርዳት ብርቱ ፍላጎት ሲያድርብኝ እግዚአብሔር ያ የእርሱ ንግግር እንደሆነ አስተማረኝ፡፡ እግዚአብሔር መልካም ስሆን ከእርሱ ጋር ጊዜ ወስደን በጥሞና ስንሆን ሌሎችን የመርዳት ፍላጎት ያድርብናል፡፡ በእያንዳንዱ ቀን እግዚአብሔር ማንን መባረክ እንዳለብህና ያም ደግሞ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ያሳደረው ፍቅር እንደሆነ አስተውል፡፡ (1 ዮሐ 4 12 ተመልከት)


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በማንኛውም አጋጣሚ ተጠቅመህ መልካም ማድረግ አለብህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon