መንፈሳዊ ሥጦታን ፈልጉ

የፀጋ ሥጦታም ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፣ አገልግሎቱም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፣ አሠራሩም ልዩ ልዩ ነው ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር አንድ ነው፡፡ 1 ቆሮ 12÷4

መንፈሳዊ ሥጦታን ማስረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም የምሰራው በመንፈሳዊ ዓለም ላይ ስለሆነ ነው፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት ጥሞናዎቼ ውስጥ በቂ ገለፃና መሠረታዊ ለሆኑ ተልዕኮዎቼ በተስፋ ስፀልይ ነበርኩ፡፡ ስለመንፈሳዊ ሥጦታዎች በጣም ብዙ የሚባሉት ርዕሶች ስላሉ ስለመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስጦታዎች የተፃፉ ጥሩ ጥሩ መጽሐፍት እንድታነብ አበረታታሃለሁ፡፡ በመለኮታዊ ዓለም ስናገለግል ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ነገር ግን ልንፈራ አይገባንም፡፡ ሰይጣን ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔርን እውነተኛ ሥጦታ በማጣመም በመለወጥና ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር ያቀርባል፡፡ ነገር ግን እኛ በፀሎትና እውነትን ከእግዚአብሔር ቃል በመፈለግ በትክክለኛው መንገድ ላይ ፀንተን መቆየት እንችላለን፡፡

ስለመንፈሳዊ ሥጦታዎች መፀለይ እንድትጀምር ላስገነዝብህ እፈልጋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ፀጋዎች እርሱ እንደፈቀደ እንዲጠቀምብህ ጠይቀው፡፡ አንተን በጣም የሚስብህን ወይም የሚያስደስትህን ሥጦታ አትፈልግ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአንተ ያለውን ፈልግ፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ በሕይወታችን እንዲሰራ ከፈቀድንለት በእለት እለት ሕይወታችን ይረዳናል፡፡ እንዲሁም በእኛ በኩል ለሚያምኑት የክርስቶስን ኃይልና መልካምነት እንዲመለከቱ ያደርጋል፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ ይኖራል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ በሕይወታችን ሲሰራ የተሰጠንን የእግዚአብሔር ፀጋ ተስፋ ለቆጡ እምነታቸውን በኢየሱስ ላይ እንዲያደርጉ የተሰጠንን የእግዚአብሔር ፀጋ ከእኛ ወደ እነርሱ ያንፀባርቃል፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ ለእራስህ መታነፅና ለሌሎች መልካም እንዲሆን በሕይወትህ እንዲሠራ ፈልግ፡፡ የፀጋውን ሥጦታ በፈለክ መጠን በይበልጥ በፍቅር ለመመላለስ መፈለግን አትርሳ ምክንያቱም ፍቅር ከስጦታዎች ሁሉ የበለጠ ስለሆነ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሥጦታ የዕለት ተዕለት መደበኛ የሕይወትህ አካል መሆን አለበት፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon