መንፈስ ቅዱስ መሪነቱን እንዲወስድ ፍቀድለት

መንፈስ ቅዱስ መሪነቱን እንዲወስድ ፍቀድለት

ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተም ርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ ኢሳ 48፡17።

ብዙ ሰዎች እንደሌላው ሰው ለመሆን ይፈራሉ። ብዙዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ከመመራት ይልቅ በ ተቀመጠውን ህግና መመሪያ ተከትለው መኖርን ይመርጣሉ። ሰዎች ያወጡትን መምሪያ ተከትለን የም ንጓዝ ከሆነ ሰዎችን እናስደስታለን። ነገር ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ የምንከተል ከሆነ፣ በእምነትም የምንራመድ ከሆነ፣ የምናስደስተው እግዚአብሔርን ነው። በተወሰነ መንገድ (ዘዴ) ለተወሰነ የጊዜ ርዝ ማኔ ለመጸለይ በውስጣዊ ስሜታችን መገፋፋት አያስፈልገንም ወይም በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ የለብንም። ምክንያቱም ሌሎችም ሰዎች ይህን ስለሚያደርጉት ነው። ከዚህ ይልቅ ግን እግዚአ ብሔር ለመጸለይ ባስተማረን ልዩ የራሳችን መንገድ በነጸነት ራሳችንን መግለጥ ያስፈልገናል። እግዚአብ ሔር ስለተለያዩ ነገሮች እንድንጸልይ ይጠቀምብናል። እንዲሁም ይህ መንገድ ሁሉምን ነገሮች ለመዳሰ ስ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ስናደርግ ለተወሰኑ ጊዜያት ምቾት ይሰማናል። ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር በውስጣችን ያለመሳካት ያለመርካት ስሜት ይሰማናል፤ ምክንያቱም ጀልባዋን ከወደቧ ፈትተን ማላቀቅ የሚለውን እስክንማር ድረስ ነው። ይህ ማለት የመንፈስ ቅዱስን ውቅያኖስ እርሱ ወደ ሚፈልገው ሥፍራ እስኪወስደን ድረስ ነው።

እኔ ለብዙ ዓመታት ሌሎች ሰዎች ያስተማሩኝን የተለዩ የጸሎት መርሆዎችና መመሪያዎችን ተከትዬ ራሴን ከወደቡ ጋር አስሬ ነበር። ይህ በመጀመሪያ መልካም ነበር፤ ነገር ግን በመጨረሻ የራሴ የጸሎት ልምምድ በጣም ደረቅና አሰልቺ ሆነብኝ። እኔም የራሴን ጀልባ ከወደቧ ላይ ማላቀቅን ስማር ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ራሴን ሰጠሁ። በህይወቴም መታደስና አዳዲስ ነገሮች መከሰት ጀመሩ፤ ይህም አስደናቂ ነበር። ሁልጊዜ ማለት ይቻላል በምጸልየው ጸሎት የሰዎችን ህግና መምሪያ እንዲሁም የተወሰኑ የሰት ገደብ ትቼ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ሳገኝ እርሱ በተለየ መንገድ ይመራኝ ጀመር።

እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ ለአንተ የሰጠውን ማንነትህን እንዲያሳይህ፤ እንዲሁም በእርሱ ቸርነት አንተን በፈጠረበት አስደናቂ መንገድ የእርሱን ድምጽ መስማትና እርሱን ለመከተል እንዲረዳህ አሁኑኑ በጸሎት ጠይቀው።


ሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ጀልባህን ከታሰረችበት ወደብ ፍታውና እግዚአብሔር ወደፊት እንዲመራህ ፍቀድለት።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon