ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ፡፡ ዮሐ. 7÷24
የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ግልፅ፣ የተመጠነ ቃል እግዚአብሔር ለእኛ የሰጡ ሰዎችን በውጭ አቋማቸው ወይም ከላይ በምታይ እንዳንፈርድባቸው ይነግረናል፡፡ ለዓመታት በቁጣና በችሎታ የምፈርድ ዓይነት ሰው ነበርኩ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ጉዳይ በጽናት መፍትሄ ለማግኘት በመሥራት በመጨረሻ እኔም በችኮላና በውጫዊ እይታ መፍረድ ምን ዓይነት አደጋ እንዳለው ተገነዘብኩ፡፡ በሰዎች ላይ ከመፍረዳችን በፊት ጊዜ በመውሰድ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ ማወቅ አለብን፡፡ አለበለዚያ አንድም በእርግጥ ያልሆኑትን ለመምሰል የሚልጉትን ሰዎች እንደሆኑ አድርገን እናፀድቃለን፡፡ ሲቀጥል ደግሞ በውጭው በኩል ከሚታይ ገፅታ ወይም እንቅስቃሴ አለመምሰል ብልም ነገር ግን በውስጡ ጠንካራና ምርጥ ሆኖ ሳለ አለማጸደቅ ወይም መጣልን ሊያስከትልበት ይችላል፡፡ እኛ ሁላችን ትንሽ እንግዳ አመል ወይም ልማድ ይኖረናል፡፡ የእኛ ለየት ያለ እንግዳ ተግባር ባሕሪና ለሌሎች በቀላሉ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ሁኔታዎች አሉብን፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በውጭ እይታ አይፈርድም፡፡ እኛም የእርሱን ምሣሌ ልንከተል ያስፈልጋል፡፡
ሰዎች ውጫዊውን ነገር በማየት ፈርዶ ብሆን ዳዊት ንጉሥ ለመሆን ባልተመረጠ ነበር፡፡ የገዛ ቤተሰቦቹ እንኳ ችላ ብሎት ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የዳዊትን ልብ አይቶ ነበር፡፡ ለበጎች የነበረውን የእረኝነትን ልብ፡፡ ለእግዚአብሔር የአምልኮ ልብ እንዳለው እርሱም የሚፈልግ ልብ እንዳለው አይቶ ነበር፡፡ ቅን ልብ ያለውና ቶሎ የሚመለስ ወይም የሚቀና ቅን ልብ ያለው ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሚመርጠው መመዘኛዎቹ እነዚህ ዓይነት ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ በውጭ እይታ ላይ ሁልጊዜ የሚታዩ ወይም የሚገኙ አይደሉም፡፡
መንፈስ ቅዱስ ስለሰዎች እንዲናገርህና እግዚአብሔርን እንድትፈልግ አበረታታሃለሁ፡፡ እርሱ ልባቸውን ያውቃል፡፡ ስለዚህ እርሱ ከማን መጠንቀቅ እንዳለብህ ወይም ከማን ጋር ኅብረት ማድረግ እንዳለብህ ይነግርሃል፡፡ ሰዎችን እንድታገኝና ከእነርሱ ጋር ኅብርትን ለማሳደግ እንዲመራ እርሱን ታመን የእራስህን ውሳኔ አይደለም፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ሰዎች ለአንተ እንዲኖራቸው የምትፈልገውን ዓይነት ፀባይ ወይም ሁኔታ አንተም ለእነርሱ ሊኖርህ ይገባል፡፡