የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኀይል መንፈስ፣ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ – ኢሳያስ 11፡2-3
ኢየሱስ በማስተዋል ነው የኖረው፡፡ የእርሱ ማስተዋል ተራ በሆነ የስጋው ምሪት እና ስሜት ሳይሆን ምንጩ ብርቱ ከሆነው ከአባቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እና ሕብረት ነበር፡፡ በተመሳሳይ የማስተዋል ስጦታ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት እና ሕብረት ውስጥ ለእኛም ቀርቦልናል፡፡
እንዴት ነው የሚሰራው? የትኛውንም ነገር ለመስራት ከመነሳትህ አስቀድመህ ውስጥህ ልታደርግ ያለህው ነገር ተገቢ መሆኑን ፈጥነህ መጠየቅ ይኖርብሃል፡፡ ሰላም ከተሰማህ ወደ ፊትህ መሄድ ትችላለህ፡፡ ምቾት ካልተሰማህ ግን ወይም ግራ ከተጋባህ እና መረጋጋት ካልተሰማህ ምንም ከማድረግ ታቀብ፡፡
ለምሳሌ ወደ ገብያ ስፍራ ሄጄ ለመክፈል ተቃርቤ እንኳን ሳለሁ ውስጤ ሲረበሽ እና መንፈስ ቅዱስ እንድገዛ አለመፈለጉን አስተውላለሁ፡፡ ይህን መሰል ገጠመኞች የመንፈስ ቅዱስን የውስጥ ንግግሩን ለመስማት ስንመርጥ የሚያጋጥመን ነው ፤ ይህንንም ባደረግን ቁጥር የእግዚአብሔር ኃይል በመንፈስ ፍሬዎች አማካኝነት በእኛ ላይ ይለቀቃል፡፡
ለመንፈስ ቅዱስ ድምጽ በመሰጠት እርሱን ተከተሉ በዚህም በማስተዋል ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ እኛም እንመላለሳለን፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ከስጋዬ ስግብግበነት እና ለታይታ የሆነ ውሳኔን መወሰን አልፈልግም፡፡ በማስተዋል መመላለስ እፈልጋለሁ፡፡ ከአንተ ያለሆነ ፍላጎቴንና ምርጫዬን አስጥለኝ ፤ ሰላምህን በመስጠት መንገድህን እንድከተል እርዳኝ፡፡