በኢየሱስ ስም ውስጥ ያለው እጅግ ታላቅ ሀይል

በኢየሱስ ስም ውስጥ ያለው እጅግ ታላቅ ሀይል

ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤ይኸውም በሰማይና በምድር፣ከምድርም በታች.ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣ኢየሱ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው፡፡ – ፊሊጲ 2፡9-11

ዙ ሰዎች ክርስቲያኖችን ጨምሮ በክርስቶስ ስም ውስጥ ስላለው እጅግ ብዙ ሀይል ሀሳቡም የላቸውም፡፡

የስምን ጥቅም አስባችሁ ታውቃላችሁ? የሰው ስም ከሌላው ሰው በመለየት ባህሪውን እና ማንነቱን ይወክላል፡፡አንድን ሰው በስሙ ስንጠራው  ስለዛ ሰው የሆነ ነገር እያወጅን ነው፡፡

በተመሳሳይ መንገድ የኢየሱስን ስም ስንጠራ ስም ብቻ እየጠራን አይደለም፡፡ሀይልን ነው፥ የሰው ሃይልን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሀይል እና ስልጣን የያዘ ስምን እያወጅን ነው (ቆላ.2፡9-10) ።

ያንን ስም ስንጠራ ያንን ሰው እየገለጽነው ነው፡፡ኢየሱስ ማለት “አዳኝ” ማለት ነው እናም እየጠራን ያለነው ለእኛ ባደረገው ነገር መሰረትነት ነው፥ ከሀጢያት፣ከውድቀቶቻችን እና ከሁኔታዎቻችን አድኖናል (ማቴ.1፡21) ።

ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ሀይልን መለማመድ ይፈልጋሉ፥ ነገር ግን እሱን ሃይል ለመልቀቅ የኢየሱስን ስም በእምነት መጥራት እንዳለባቸው ነው፡፡ይህ አስደናቂ ስም ለሚያምኑ ሁሉ ተሰጥቷል፡፡እንደ እግዚአብሔር ልጅ ዛሬ ስሙን በእምነት ጥሩ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

አባት እግዚአብሔር ሆይ በህይወቴ በሚያጋጥሙኝ ነገሮች ሁሉ የኢየሱስን ስም በእምነት አውጃለሁ፡፡ስለልጅህ የማዳን ሀይል አመሰግንሀለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon