ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ

ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ

ሕግ ሁሉ (የሰው ልጆችን ግንኙነት በተመለከተ) በአንድ ትዕዛዝ የታሰረ ነው፤ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ (ገላትያ 5: 14)

እግዚአብሔር ስለ ብዙ ነገሮች ሊናገረን ይፈልጋል፣ ነገር ግን እኛን ሊናገረን ከሚፈልገው ወሳኝ ነገሮች አንዱ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት በተመለከተ ነው። እግዚአብሔር ይወደናል፤ እናም እኛ ጤናማ እና ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ እራሳችንን እንድንወድ ደግሞም የእርሱ ፍቅር በእኛ በኩል ወደ ሌሎች ሰዎች እንዲፈስ ይፈልጋል።

ከእግዚያብሔር ዘንድ ለመስማት በምትዝጋጅበት ጊዜ ግንኙነቶችህን በተመለከተ ለአንተ ያለውን ማንኛውንም ጥበብ በየጊዜው እንዲናገርህ እንድትጸልይ እለምንሃለሁ። ግንኙነቶች ትልቅ የሕይወት ክፍል ናቸው እናም ጥሩ ካልሆኑ የህይወታችን ጥራቱ እየተበላሸ ይሔዳል። ዛሬ ጠዋት ለባለቤቴ እየጸለይኩ ነበር እናም ምን ላደርግለት እንደምችል እግዚአብሔርን ጠየኩት። ቁርስ ሊበላ ማዕድ ቤት ሲመጣ የሚያገኘውን ማስታወሻ ልተውለት የሚል ሀሳብ ነበረኝ። ማስታወሻው በቀላሉ እንዲህ ይል ነበር። “ደህና አደርክ ዴቭ? … እወድሃለሁ !!!” ከስሩ ፈገግታን የሚያሳይ ምስል አስቀምጬ ፊርማዬን አኖርኩበት። ማስታወሻውን ለመተው የመጣልኝ ሀሳብ እግዚአብሔር የተናገረኝ እንደነበር እና ያንን ትንሽ ነገር ለማድረግ መታዘዜ ግንኙነታችንን አሻሽሎት እንደነበር አምናለሁ።

ስለሁሉም ግንኙነቶችህ መጸለይ ጀምር። አንድ በአንድ ዉሰዳቸውና የተሻሉ ግንኙነቶች እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንደምትችል እግዚአብሔርን ጠይቅ። ብዙውን ጊዜ ሌሎች ሰዎች ለእኛ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እናስባለን፤ ነገር ግን የፍቅርን ህግ የምንከተል ከሆነ ከራሳችን ይልቅ ለእነሱ አብልጠን እናስባለን።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ግንኙነቶችህን እንዴት የተሻሉ ማድረግ እንደምትችል እግዚአብሔር እንዲያሳይህ ጠይቀው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon