ትንቢት የመናገር ሥጦታ

ትንቢት የመናገር ሥጦታ

ለአንዱም ትንቢትን መናገር (መለኮታዊ ፈቃድና ዓላማ የመተርጎም ፀጋ) .. 1ኛ ቆሮ 12 ÷10

እውነተኛ የትንቢት ፀጋ ሥጦታ የሚሠራው የሆነ ሰው ከእግዚአብሔር ግልፅ መልዕክት ሰምቶ ለሆነ ሰው፣ ቡድን፣ ወይም ለሁኔታ ስናገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትንቢት በጣም ጥቅል ወይም አጠቃላይ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የተወሰነ ነው፡፡ የምመጣው ደግሞ በተዘጋጀ መልዕክት (በእግዝአብሔር ቃል ስብከት) ወይም በመለኮታዊ መገለጥ በኩል ልመጣ ይችላል፡፡

ምንም እንኳ የትንቢት ሥጦታ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ሁከትና ግራ መጋባት ሲፈጠርበት ይታያል፡፡ ፍጹም እውነተኛ ነብያቶች በዚህ ዘመን አሉ፡፡ ነገር ግን የዛኑ ያህል ሃሰተኛ ነብያቶችም አሉ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር የሆነውን ቃል የምናገሩ ምንም ጉዳት የለውም፡፡ ነገር ግን ከእራሳቸው አእምሮ፣ ፈቃድና ስሜትን ከእግዚአብሔር መንፈስ አስመስሎ የምናገሩ እነርሱ ውከትና ጥፋት ያስከትላሉ፡፡

የእውነተኛ የእግዚአብሔር ትንቢት ዓላማና ግቦች የእግዚአብሔርን ሕዝብ መገንባትና ማነጽ እንዲሁም በመንፈሳዊ ሕይወት ማበረታታትና ማጽናናት ነው፡፡ (1 ቆሮ 14÷3 ተመልከት) ሁሉም የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች ለሁሉም ለመልካምና ለጥቅም ነው የተሰጡት፡፡ በተጨማሪም እውነተኛ ቃል ከእግዚአብሔር መሆኑ የሚረጋገጠው ሠላምና መረጋጋትን ለልባችን በመስጠት ነው አንድም በሆነ ነገር ለልብህ ማረጋገጫ ይሰጥሃል፡፡ ምንም እንኳ ነገሩ ግልፅ ባይሆንም፡፡ እነዚህ መሥፈርቶች ትንቢቶች እውነተኛ ይሆኑ ወይም አይሁኑ ለመወሰን ይረዳል፡፡ በእርግጥ ትክክለኛ የትንቢት መመዘኛው በመፈፀምና ባለመፈፀም የሚመዘን ቢሆንም ይህንን አስታውስ እውነተኛ ትምቢት ይፈፀማል፡፡

የትንቢት ፀጋ ያላቸው ግለሰቦች ብቻ ከእግዚአብሔር የሚሰሙ አይደሉም፡፡ አንተም የእግዚአብሔርን ድምፅ ለራስህ የመስማት መብትና ችሎታ አለህ፡፡ ስለዚህ በልብህ እውነተኛ ትንቢቶችና እውነተኛ ያልሆኑትን ለማረጋገጥ ሁልጊዜ ከሚነገሩት ትንቢቶች ጀርባ ያለውን መንፈስ ለመለየት ጥረት በማድረግ ትንቢቶችን በመቀበል መርምር፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ሰዎች ስመክሩና ከእግዚአብሔር የሆነ ድምፅ ስነግሩህ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መስማቱንና የልብህን ምስክርነት እርግጠኛ ሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon