
አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ፣ አዲስም መንፈስ በውስጣቸው እኖራለሁ፣ የድንጋይንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፣ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ፣ መንፈስንም በውስጣችሁ እኖራለሁ፣ በትዕዛዜም አስኬዳቸዋለሁ፣ ፍርዱንም ትጠብቃላችሁ፣ ታደርጉትማላችሁ፡፡ ሕዝ 36÷26-27
የዛሬው ጥቅስ የያዘው የእግዚአብሔር ተስፋ ከብዙ ሺህ አመታት በሬት ለሰዎች አዲስ ልብ የምሰጥበት ጊዜ እንደሚመጣና የእርሱን መንፈስ በእርሱ ውስጥ የምንኖርበት ተስፋ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይህንን የተስፋ ቃላት ስናገር ሰዎች ይተዳደሩበት የነበረው ለብሉዕ ክዳን ሕግ ነበር፡፡ ከኢየሱስ መወለድ መሞትና ትንሳኤ በሬት ነበር፡፡ በዚያ በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ላይ ለተለየ ዓላማ ይመጣ ነበር፡፡ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ አይኖርም ነበር፡፡
እኔና አንተ ያለነው በአዲስ ክዳን ዘመን ነው፡፡ እግዚአብሔር በነብዩ ሕዝቄል መንፈስ ቅዱስን በመላክ በእኛ ለማዳን የገባውን ተስፋ የሚፈፀምለት ዘመን ላይ ነው ያለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እስኪነሣ ድረስ ደግሞ የተወለደና መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ዘንድ ማደሪያ ያደረገ ማን ሰው አልነበረም፡፡ አሁን እርሱ ስለመጣ እኛ እርሱን እንደ ጌታና አዳኝ ስንቀበል መንፈስ ቅዱስን በልባችን መቀበል እንችላለን፡፡ እርሱ በእኛ ውስጥ ሲኖር እርሱ ለእኛ ይነግረናል፡፡ የእርሱን ድምፅ እንድንሰማ ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ኃይልን ይሰጠናል፡፡ እርሱ የሚለንን ለማድረግ እንድንችል ያደርገናል፡፡
እኔ በጣም የሚያስደንቅ በረከት የሆነውን የእግዚአብሔር የተመረጠ ማደሪያ መሆንህን እንድታሰላስለው አበረታታሃለሁ፡፡ ያም ማለት አንተና እግዚአብሔር የተቀራረብክና ከእርሱ ጋር ባለ ኅብረት ደስተኛ መሆንህን ተስፋ እንድታደርግ ነው፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- አንተ በእግዚአብሔር በጣም ቅርብ ነህ፡፡