ኢየሱስ በተመላለሰበት ሞገስ ተራመዱ

ኢየሱስ በተመላለሰበት ሞገስ ተራመዱ

ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር፡፡ – ሉቃስ 2፡52

ኢየሱስ ከልጅነቱ ጀምሮ በሰው እና በእግዚአብሔር በልዕለ ተፈጥሯዊ ሞገስ ይራመድ ነበር፡፡ በእርግጥ ብዙ ተከታዮች ስለ ነበሩት ብቻውን ለመሆን ፣ ለመጸለይና ከአባቱ ጋር ሕብረት ለማድረግ ይቸገር ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ የማያምኑበት ጭምር ክርስቶስ በእግዚአብሔር ሞገስ ይመላለስ እንደነበር ተገንዝበዋል፡፡

ኢየሱስን እንዲያስሩ የተላኩ ሎሌዎች፤ ሳያመጡት ቀርተው እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም ብለው ተናግረዋል (ዮሐ 7፡46 ) ፡፡ እስከ ሕይወቱ ማብቂያ ብሎም በመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ እንኳን ሰዎች እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ተገንዝበዋል( ሉቃስ 23፡47-48)፡፡

ይኸው ሞገስ ዛሬ ለእኛም ተዘጋቷል፡፡ የሆነው ሁሉ ቢሆን ይህን ፈጽሞ መዘንጋት የለብንም በሰው እና በእግዚአብሔር ፊት እኛም ሞገሰ ይኖረናል፡፡ ( ሉቃ 2፡52 ይመልከቱ) በርካታ ነገሮችን ከእግዚአብሔር እንቀበላለን ብለን እንደምናስበው ሞገሱም ከእርሱ እናገኛለን ፡፡

ዛሬ በእምነት ኑሩ ፣ በኢየሱስ ላይ የነበረውን ዓይነት ሞገስ እግዚአብሔር እንደሚሰጣችሁ ደፍራችሁ ጠብቁ፡፡ በሕይወታችሁ ከመጣው ከየትኛውም ዓይነት ሁኔታ በላይ እግዚአብሔርን ለልዕለ ተፈጥሯዊ ሞገስ እመኑት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ኢየሱስ የተመላለሰበት ያ ሞገስ ለእኔም እንደ ቀረበልኝ አውቃለሁ ፤ በሰው እና በአነት ፊት ስመላለስ ይህ ሞገስ አንዲኖረኝ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon