ኢየሱስ የመጣበት ምክንያት

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።ያዕ 4:8

ላይ ስላለዉ ጥቅስ አንድ ነገር ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡ ኀጢአትን ማድረግ እንድናቆም ከመታዘዛችን በፊት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ እንደታዘዝን ልብ በሉ፡፡

ብዙ ሰዎች አሉ ይህን ገለባብጠዉ የያዙት፡፡ ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ መምጣት እንደማይችሉ ያስባሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ እንደማይችሉ ያስባሉ፣ ፈጽሞ ክርስቲያን መሆን እንደማይችሉ ያስባሉ ምክንያቱን ከዚያ በፊት በህይወታቸዉ መፍታትና ማሸነፍ ያለባቸዉ ጉዳዮች እንዳሉ ያስባሉና ነዉ፡፡ ከእርሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ ቀድመዉ ማድረግ ያለባቸዉ ነገር እንዳለ በማሰብ ይወጠራሉ፡፡

ነገር ግን ያ ስህተት ነዉ፡፡ ኢየሱስ የመጣበት ምክንያት እኛ ያለ እርሱ በቂ መሆን ስለማንችል ነዉ፡፡ ኢየሱስን በህይወታችን ልንይዘዉ ይገባል፡፡ ሞቱ፣ የፈሰሰዉ ደሙ ለእኛ ሀጥያት የተከፈለ ነዉ ዕዳችንን የከፈለ ነዉ፡፡

በኢየሱስ ስም በኩል ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ ዉጪ ወደ እርሱ የምንቀርብበት እና ከሀጥያት የምንጸዳበት ሌላ መንገድ የለም፡፡ እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንድትቀርብ ዛሬ ይፈልጋል፡፡ ኀጢአትህን ቀድመህ ማንጻት አለብህ የሚለዉን ዉሸት አትስማ ዉጪ አትቁም በምትኩ ወደ እግዚአብሔር ሂድ እርሱም በክርስቶስ መስዋዕትነት ኀጢአትህን ያስወግደዉ፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ኀጢአቴን በሚያስወግደዉ በኢየሱስ ደም በኩል ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለ ይቅርታህ አመሰግንሃለሁ፡፡ ወደ አንተ መቅረብ ፍቅርህንና ይቅርታህን መቀበል እንደምችል ስለማዉቅ ኩነኔዬን  አስወግጄ ወደ አንተ እመጠለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon