እጅግ በጣም የምበልጥ መንገድ

እጅግ በጣም የምበልጥ መንገድ

ነገር ግን የምበልጠውን የፀጋ ሥጦታ በብርቱ ፈልጉ፡፡ ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ፡፡ 1 ቆሮ 12÷31

አንደኛ ቆሮንጦስ ምዕራፍ 13 የዛሬው ጥቅሳችንን በማስቀደም የምንጀምረው በግልፅ የሚነግረን ምን ያህል ብዙ የፀጋ ሥጦታዎችን መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ እንዲሰራ ማድረጉ ችግር የለውም፡፡ እነዚህ ፀጋዎች በሕይወታችን በፍቅር የማንሰራበት ከሆነ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ በዛሬ ጥቅሳችን መሠረት ፍቅር ከማንኛውም ነገር በላይ እጅግ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡

በሰዎችና በመላዕክት ቋንቋ ብንፀልይ እንኳ የነብይነት የላቀ ችሎታዎች ቢኖረን ምስጥራትን ብንረዳ እውቀት ሁሉ ቢኖረንና ተራራን የሚያንቀሳቅስ እምነት ቢኖረን ነገር ግን ፍቅር ከሌለን እኛ ምንም አይደለንም፡፡ (1 ቆሮ 13÷2 ተመልከቶ) በመንፈስ ቅዱስ በመሞላቴ ቀናት አካባቢ ከእግዚአብሔር ጋር በነበረኝ ንግግር ስለ መንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስጦታ ብዙ የሰማሁት ንግግሮች ነበሩ፡፡ ብዙ ሰዎች የሚያተኩሩት ሊኖሩአቸው የሚፈልጉትንና እንዴት እንደሚለማመዱት ላይ ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ስለፍቅርና ስለሌሎች የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ይልቅ በብዛትና በስፋት የሰማሁት ስለመንፈሳዊ ፀጋ ሥጦታዎች ነበር፡፡

በ1ኛ ቆሮንጦስ ምዕራፍ 12 ላይ ዘጠኝ የፀጋ ሥጦታዎች እና በሮሜ መልዕክት ምዕራፍ 12 ደግሞ ብዙ የፀጋ ሥጦታዎች ተዘርዝረዋል፡፡ በገላቲያ መልዕክት ምዕራፍ 5 ዘጠኝ (9) የመንፈስ ፍሬዎች ተዘርዝረዋል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስጦታዎች እጅግ በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ እኛም በጥልቀት ልንሻቸው ያስፈልጋል፡፡ ስለእነርሱም ልንማር ያስፈልጋል፡፡ በእነርሱም እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለብን ልናውቅ ይገባል፡፡ የተሰጡንን የፀጋ ስጦታዎችን እንዴት መንከባከብ እንዳለብን ልናውቅ ይገባናል፡፡ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ስጦታዎችን ወይም በፀጋዎቹ እንዴት መጠቀም የምንችልበት ችሎታ በምንም መልክ ቢሆን ከመንፈስ ፍሬ ከሆነው ከፍቅር አግዝፈንና አስበልጠን ማየት የለብንም፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እግዚአብሔር ይወድሃል፡፡ እንዲሁም ለሌሎች የራሱን ፍቅር በአንተ በኩል ወደ እነርሱ እንዲፈስ ይፈልጋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon