እግዚአብሔርን አታስቆጣው

እግዚአብሔርን አታስቆጣው

‹‹ … ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ›› (ፊሊ.2፡12) ፡፡

መንፈስ ቅዱስ ህይወታችንን ሁሉ እንዲቆጣጠር መፍቀድ አለብን፡፡ በእርሱ ህልውናና ኃይል በመሞላት በሁሉም የህይወታችን ክፍል ላይና በምናደርገው ሁሉም ነገር እርሱ እንዲገዛ መፍቀድ አለብን፡፡እርሱ ሃሳባችንን፣ ስሜታችንንና፣ ፈቃዳችንንም ጭምር በማግኘት ለሁለንተናችን ፈውስንና ጤንነት ለመስጠት ይችላል፤ እርሱ ዛሬም ይጋብዝሃል፡፡

እርሱ ወደፊት ባለው ህይወትህ በእግዚአብሔር ጸጋ አንድ ነገር እንዲሠራና አንተም ከእርሱ ጋር እንድትሠራ፣ ዝግጁ እንደሆንክ ለመንፈስ ቅዱስ ተናገር፡፡ የዛሬው የቅዱሳት መጽሐፍት ዋና ሀሳብ ‹‹ሥራህን ፈጽም›› የሚለው ሲሆን ይህም ማለት ለመኖር ከመንፈስ ቅዱስ መማር ማለት ነው፡፡ ከውስጥ ወደ ወጪ የሚመነጭ ህይወት ለመኖር ማመር አለብን፡፡ እግዚአብሔርን በኃጢአትና በፈተና ከማስቆጣት እንጠንቀቅ፡፡ በዚህ ዓይነት ህይወት በመኖር ህሊናችን ሙሉ በሙሉ ንጹህ እንዲሆን ማወቅ አለብን፡፡

ምናልባትም ‹‹ጆይስ የምታነገሪው ይህ ሁሉ ነገር ከባድ ነው፤ አንዱንም ለመቀበል እንድችል እርግጠኛ አይደለሁም›› ብለህ ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እርግጠኛ እንድትሆን የምፈልገው ነገር ቢኖር የምትወስደው ነገር ይኖራል፤ ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአንተ ህይወት ውስጥ ይኖራልና፡፡ በራስህ ብርታት ምንም ማድረግ አትችልም፤ ነገር ግን በህይወትህ ማንኛውንም እንድታደርግ የሚስፈልግህን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር አጋር ከሆንክ ልታደርግ ትችላለህ፡፡ የተትረፈረፈ ህይወት እየጠበቀህ ስለሚገኝ ‹‹በትንሽ ባገኘኸው›› ነገር ተረጋግተህ አትኑር፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ አግዚአብሔርን ከሚስቆጣ ማንኛውም ነገር ተመለስ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon