እግዚአብሔር ሲናገር …

እግዚአብሔር ሲናገር …

‹‹ … የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል›› (ዕብ.4፡12) ፡፡

የእግዘአብሔር ቃል በትክክል በእኛ ህይወት እንድሚሠራ መናገር እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር ዕቅድ በህይወታችን እንዳይሰራ የሚከላከሉትን ነገሮች ከህይወታችን ቆርጦ ያነሳዋል፡፡ በህይወታችን ውስጥ ያሉትን ሥጋዊ ነገሮችን ሁሉ በመለየትና በማሳየት በመንፈስ ቅዱስ ከህይወታችን ያስወግደዋል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ተማሪ በሆነኩበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ከራሴ ነፍስ (ማለትም ከአዕምሮ፣ ፈቃዴና ስሜቴ) መስማትና በትክክል በመንፈስ ቅዱስ ከመመራት መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት ምንም በቂ የሆነ ልምምድ አልነበረኝም ነበር፡፡ አንድ ነገር ለማድረግ ስፈልግ፣ አንድ ነገር እንዲሆን ብዬ ለማድረግ እሞክርና ካልሆነ ከዚም እቆጣለሁ አዝናለሁ፡ እኔ በዚህ ጊዜ ራስ ወዳጅ፣ ስጋዊ ነበርኩ፤ ከዚያም ከዓመታት በኋላ እግዚአብሔር ቃሉን በመጠቀም በህይወቴ እየሠራና ስህተት የሆኑትን ባህሪያቴን ቆርጦ አስወገደው፡፡

ማንኛውም የቀዶ ጥገና ህክምና ነማንንም አያስደስትም፤ ነገር ግን በመልካም ጤንነት ላይ ለመገኘት ግን እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር ከህወትህ አንድ ነገር ለመቁረጥ እየጣረ ይሆንን ይህ የሚያምም ነውን አብዛኛው የቀዶ ጥገናዎች አይመቹም ነገር ግን በቆይታ ውስጥ ግን የሚረዱን ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በህይወትህ የተሻለ ነገር እንዲሠራ ከፈለግህ በመንፈሳዊ ህይወትህ እንዳታድግ የሚያደርግህን ነገሮች ሁሉ ካንተ ህይወት እንዲያስወግደው መፍቀድ አለብህ፡፡ ለመንፈሳዊ ህይወት ዕድገት (ብስለት) ምንም ዓይነት አቋራጭ መንገድ የለም፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ለስኬት ያለው ረጅም መንገድ ጥበብን ሊሰጠን የሚችል ጠቃሚ ትምህርቶችን የምንማርበት አንድ ነገር ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon