
“ሃሌ ሉያ! እግዚአብሔርን የሚፈራ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድ ሰው ምስጉን ነው፡፡ ከክፉ ነገር አይፈራም በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የፀና ነው፡፡ መዝ፡ 112፡ 1÷7
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ጥልቅ የልብ ሠላም በመስጠት ይናገራል፡፡ ሁኔታዎች ሁሉና ሁሉም ሰው እግዚአብሔርን በመታመን በሠላም እንድትሆን ይነግሩሃል፡፡ ነገር ግን እንዴት ሆኖ የሚለው ይከበሃል፡፡ ፍርሃት ከዙሪያ ሆኖ የራሳቸው ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ጓደኞችህ ደግሞ ሁሉ ነገር መልካም ይሆናል ይሉሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በጥልቀት ለልብህ እኔን ታመን እኔ በዚህ ጉዳይ ሃላፊነት እወስድልሃለሁ እስክልህ ድረስ ሌሎችን ለማመን ይከብድሃል፡፡ እግዚአብሔር ከተናገረህ በኋላ ግን ሁሉ ነገር መልካም ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በ1989 ለሕክምና ምርመራ ወደ ሐኪም ቤት ስሄድ፤ ሐኪሙ በምርመራው በፍጥነት እያደገ የሚሄድ ካንሰር እንዳለብኝ አረጋግጦ በፍጥነት ወደ ቀዶ ጥገና መራኝ፡፡ ከዚህ ዜና የተነሣ ከባድ የሆነ ፍርሃት ያዘኝ፤ መተኛት አልቻልኩም፡፡ ከወደቀብኝ ታላቅ ፍርሃት የተነሣ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ቤተሰቦቼና ወገኖቼ በብዙ መልኩ ቢያበረታቱኝም እስከ ማለዳው ሦስት ሰዓት ድረስ በፍርሃት ጦርሜዳ ውስጥ ቆየሁ፡፡ ከዚያ እግዚአብሔር ልቤ ውስጥ ጆይስ፤ እኔን መታመን ትችአልሽ፤ አለኝ፡፡
ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት የፍርሃት ስሜት ወደ እኔ አልመጣም፡፡ የሕክምና ውጠየት እስኪመጣልኝ አልተጨነኩም፡፡ ምክንያቱም የፈለገ ነገር ቢሆን በእግዚአብሔር እኛ ውስጥ ነኝ፡፡ እርሱ ለእኔ ይጠነቀቃል፡፡ ውጤቱ እንደደረሰ ሌላ ተጨማሪ ሕክምና አላስፈለገኝም፡፡ ከፍርሃት ተላቅቄ በምሥጋና ተሞላው፡፡ የእግዚብሔርን ድምፅ ለመስማት ስንማር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የሚሆነው ይሄው ነው፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንቴ፡- በእግዚአብሔር ታመን እርሱ አይጥልህም፡፡