እግዚአብሔር በጥልቀት ያውቅሃል

እግዚአብሔር በጥልቀት ያውቅሃል

«… የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ። አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ» (መዝ.139፡4)።

እኛ በግል ደረጃ ወደ እርሱ ቀርበን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ስለምናደርግ ማለትም ይህንን ህብረት እርሱ የሚፈልገው መንገድ ስለሆነ፣ እኛም በግል ወደ እርሱ በጸሎት እንቀርባለን። ልባችንን እንደ አንድ ሰው ድምጽ ከሌሎች ጋር በቀላሉ እናስማማለን። በዚህ ዓይነት የጋራ የጸሎት ጊዜ እግዚአብሔር የምንጠቀመውን ስልት ተመሳሳይ ወይም አንድ ከሚሆነው በላይ ልባችን አንድ ይሆን ዘንድ ይፈልጋል።

«ጌታ ሆይ ጸሎትን አስተምረን» ሰንል እየጠየቅን ያለነው በተለየ የግል መንገድ እንዴት እንደምንጸልይ እንዲያስተምረንና ጸሎታችን ቀለል ያለ እንዲሆን እንዳስችለን ማለትም ራሳችንን ቀለል ባለ መንገድ ለእርሱ መግለጥ ማለት ነው። ይህንን ስንል ግላዊ ማንነታችን በጸሎት ክፍላችን በር ላይ መመርመር አለብን ማለታችን አይደለም። ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ ልክ እንደተፈጥሮአዊ ማንነታችን ያለምንም ውጪያዊ ሰው ሰራሽ ነገር ማለት ነው እርሱ እኛን ሲፈጥረን እንድንሆን በፈለገው «እውነተኛ ማንነት» ከእርሱ ጋር ህብርት በማድረግ ደስተኛ እንድናደርገው ይፈልጋል። ወደእግዚአብሔር ስንቀርብ ብርታታችንን፣ ድክመታችንን፣ የተለየ ማንነታችንንና በዚህ ዓለም ስንኖር ከሌሎች ሰዎች በተለየንበት አስደናቂ በሆነው ሌሎች ጉዳዮች ሁሉ ጋር መሆን ያስፍልገናል። እግዚአብሔር ባለንበት ሥፍራ ከእኛ ጋር ህብረት ማድረግን፤ ከእኛ ጋር የግል የጠበቀ ህብረት ማሳደግን፤ እኛ እንድንሆን በሚፈልገው ሁሉ ነገር ሆነን እንድናድግ ሊረዳን ይፈልጋል። እኛ አሁን እነዳለንበት ሁኔታ ወደ እርሱ በመቅረብና በህልውናው ውስጥ በመሆን ነጻነት የሚሰማን በመሆን ይህንን የሚያነቃቃ እውነት ማረጋገጥ አለብን።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ወደ እግዚአብሔር ስትቀርብ ሰው ሰራሽ የሆነ ውጪያዊ ነገሮችን ማድረግ አያስፈልግህም።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon