እግዚአብሔር እየመራህ እንዳለ እመን

እግዚአብሔር እየመራህ እንዳለ እመን

‹‹ … በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይጠብብም በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም›› (ምሳ.4፡12) ።

እግዚአብሔር እንዴት እንደምንሰማ በሚለው የመማር ጉዞዬ ያረጋገትኩት ነገር ቢኖር እርሱ እየመራን እንዳለ በቀላሉ ማመን እንዳለብንነው፡፡ እርሱ በእርምጃዎቻችን እንዲመራን መጸለይና እኛም የጸለይነውን ነገር እንደሚያደርግ በእምነት እናምናለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጥርት ያለ ድምጽ የምሰማበት ጊዜ አለ፡፡ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ስለቀኔ በእግዚአብሔር ፊት እጸልያለሁ፡፡ ከዚያም በእምነት እጓዛለሁ፡፡ በዚያ ቀን ምንም መለኮታዊ ወይም ምስጢራዊ (መንፈሳዊ) ነገር ፈጽሞ ላሆን ይችላል፡፡ ምንም ራዕይ የለም፣ ድምጽ የለም፣ ከጊዜው የተለየ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉ መልካም እንዳደረገና መንገድን መከተል እንዳለብኝ በልቤ አውቃለሁ፡፡

እግዚአብሔር እኛ እንኳን ከማናውቃቸው ብዙ ነገሮች ጠብቆናል፡፡ ብዙውን ጊዜ በድነገተኛ አደጋ ሊያጋጥመኝ በሚችልበት በዚ ማለዳ እግዚአብሔር እንደመራኝ ጸልዬ ነበርን አስፈሪ የትራፊክ መጨናነቅ አጋጥሞኝ አምልጬአለሁ፡፡ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ የምንጠቀምበት መንገድ ትቼ ሌላ መንገድ እንድጠቀም ተሰምቶን ነበር፡፡ እንድትጸልይ ጠንካራ ምክር ልሰትህ እወዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር ለምሪቱና ለጥበቃው ጸልይ፡፡ ከዚያም ቀኑን ሙሉ አንዲህ በል፡፡ እኔ ዛሬም ሆነ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እየተመራሁ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

መዝ.139፡2 እንዲህ ይላል እግዚአብሔር መቀመጣችንንና መነሳታችንን ያውቃል፡፡ እርሱ በእንዳንዱ መቀመጣችንና መነሳታችን የሚያውቅ ከሆነና በቃሉ ውስጥ ስለዚሁ ነገር ሊናገረን ጊዜ የሚወስድ ከሆነ ከዚም እርሱ ስለሌሎች ጉዳዮቻችን ሁሉ ይመለከተዋል እንዲሁም ይጠነቀቃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ አግዚአብሔር በእንዳንዱ እርምጃዎቻችን በስራ ላይ እንዳለ በማወቅ በእርሱ ላ ማረፍ እንችላለን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon