እግዚአብሔር ወደ ከፍታ ልወስድህ ይፈልጋል

እግዚአብሔር ወደ ከፍታ ልወስድህ ይፈልጋል

ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው ጥበብን ያበዛል፣ ጻድቅንም አስተምረው እምነትን ያበዛል፡፡ ምሳ፡ 9÷9

እግዚአብሔር በሕይወታችን ደስተኞችና የተረጋጋን እንድንሆን ቢፈልግም ርሱ እራሱ አንዳንድ ጊዜ አለመረጋጋትን ወይም አንድ ነገር ትክክል ያልሆነ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም እርሱ አሮጌና ድግግሞሽ ሕይወት ውስጥ እንድንቀጥል ስለማይፈልግ ነው፡፡ እርሱ የሚፈልገው እኛ ጎትጉተን ወደ አዲስ የሕይወት ደረጃ እንዲስደን ነው፡፡

እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚፈልገው በብርቱ እንድናድግ፣ እንድንጠነክርና ከእርሱ ጋር ያለን ቅርበት እንድንጨምር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር ወደ ብስለት እንድንመጣ ለማድረግ ስፈልግ በፊት ከተመቻቸንበት ቦታ እንድንወጣ በማድረግ ነው፡፡ ለብዙ ጊዜያት በተመቻቸ ሥራ ቆየን ማለት ለብዙ ጊዜያት ዕድገት ማቆማችንን ያመለክታል፡፡ በልብህ የሚረብሽህና ሠላም የሚነሳ ነገር ካጋጠመህ ነገሩንም ካልተረዳህ እግዚአብሔርን በመጠየቅ በትዕግሥት መልስ እስክታገኝ ድረስ ጠብቅ፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ጊዜ ለዕድገታችንና ለብስለታችን ወሳኝ ጥቅም አለው፡፡ እኛ ሁልጊዜ አንድ ዓይነት ነገርና አንድ ዓይነት ልምድ እንድንለማመድና እንድናደርግ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ሃሳቡ አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ አሰልቺ ስለሆነብኝ እግዚአብሔር በቀላሉ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ለወራት እንዳነብ ይመራኛል፡፡ ያችው ትንሽ ለውጥ ወደ እድገት ያመጡኛል፡፡ ምክንያቱም ነገሮችን በተለየ መንገድ ለማየት ስለሚያስችለኝ ነው፡፡ ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱስን ባለማንበብ ሊከሰኝ ሲፈልግ እግዚአብሔር ደግሞ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ቅጂ እንዳነብ ይመራኛል፡፡ አንድ ቀን ለማንበብ ሆነ ለመፀለይ ሲያቅተኝ ወደሌላ ወንበር ሄጄ ስቀመጥ እንደድንገት በቢሮዬ ለብዙ ዓመታት የነበሩትን ነገሮች ለማየት ቻልኩ በፊት አላስተውላቸውም ነበር፡፡ ትንሽ ለውጥ ሁሉን ነገር በተለየ አቅጣጫ ለማየት አስቻለኝ፡፡ እግዚአብሔርም በሌላ ወንበር ላይ በተቀመጠ መንፈሳዊ መረዳት ሰጠኝ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ወንበርህን ለመቀየር አትፍራ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon