እግዚአብሔር ወዴት አለ ?

እግዚአብሔር ወዴት አለ ?

እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት። (ኢሳይያስ 55 6)

በአገልግሎት ባሳለፍኳቸው ዓመታት፣ በተደጋጋሚ የእግዚአብሔር መገኘት ለምን እንደማይሰማኝ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡

ከቅዱሳት መጻሕፍት እንደተረደነው እርሱን የሚያሳዝነውን ነገር በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደማይሸሽ እና ትቶን እንደማይሄድ (ዕብራውያንን ተመልከቱ 13፤5) እንደ እውነቱ ከሆነ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ለመጣበቅና እንድንጸና በችግሮቻችን ለመርዳት ቃል ገብቶልናል ምንም እርዳታ ሳናገኝ ትተን እንድንሄድ አያደርገንም ።

አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስ ፈጽሞ አይተወንም፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ “”ይደብቃል።”” አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከልጆቹ ጋር መሸሸጊያና መፈለግን ይጫወታል ለማለት ይወዳሉ። አንዳንዴ ከኛ ይደብቃል እስከ መጨረሻው፣ በቂ ናፍቆት ሲኖረን፣ እርሱን መፈለግ እንጀምራለን። ስንፈልገው ደግሞ ቃል ገብቶልናል እሱን እናገኘለን (1 ዜና መዋዕል 28፤9 ይመልከቱ፤ ኤርምያስ 29፤13) ።

እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ፊቱን፤የእርሱን ፈቃድ ለሕይወታችን እንድንፈልግ፤ደገግሞ ይነግረናል፡፡ መፈለግ ማለት በሙሉ ኃይልህ መሻት፣ መከተተል(መሳደድ)፣ እና መከተል ማለት ነው። እኛም ቀደም ብለን በትጋት እንድንፈልገው ተነግሮናል።እንዲሁም እርሱን በፍጥነት በትጋት እንድንፈልግ ተነገረን፡፡እግዚአብሔርን አንፈልግም ከልን፡ተስፋ የቆርጠ ሕይወት እንኖራለን፡፡ እግዚአብሔር መፈለግ እርሱ እንድናደርግ የሚፈልገው እና እንድናደርግ የሚያስተምረን አንድ ነገር ነው፡ከእርሱ ጋር የምንራመድበት ማእከላዊና ለመንፈሳዊ እድገት ነው፡፡ለአንተ ምን ያህል አስፋለጊ እንደ ሆነ እና ከእሱ ውጭ ምንም ማድረግ እንደማትችል ለእግዚአብሔር ንገር፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፤ ዛሬ በሁሉም የሕወትህ ጉዳዮች ውስጥ እንዲሳተፍ በመጠየቅ እግዚአብሔርን አክብሩ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon