ከእውነታው የራቁ መጠባበቆች አስወግድ

ለምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ቸር የለም፤ – ማርቆስ 10፡18

እውነታ የራቁ መጠባበቆች ሰላማችንና ደስታችንን በፍጥነት ይሰርቁብናል፡፡  በትንሿ ፍጹም ዐላማችን ውስጥ ፣ ፍጹም ከሆኑ ሰዎች ጋር ፣  በፍጹም ደስታ ፍጹም የሆነ ቀን ለማሳለፍ እንሻለን ነገር ግን ይህ ሊሆን የማይችል እና ከእውነታው የራቀ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በእውነታው እግዚአብሔር ብቻ ፍጹም ነው፡፡ ከእርሱ ውጭ ያለው ሁሉ በግንባታ ሂደት ውስጥ ነው፡፡

ከእውነታው የራቀው መጠባበቃችን ሲፈርስ ሰላማችንን እንደሚሰርቅ ዲያቢሎስ ስለሚያውቅ ሊያበሳጨን ይነሳል፡፡  ዲያቢሎስ ለበረካታ  ዓመታት ሰላሜን እንዲሰርቅ ከፈቀድኩለት በኋላ ሕይወት ፍጹም እንዳልሆነች ተረዳሁ ፤ ነገሮቻችንም ባላቀድናቸው መንገድ ሊሄዱ እንደሚችሉ ተገነዘብኩ፡፡ አዲሱ አቋሜ  በቃ ሕይወት ይህ ነው የሚል ሆነ፡፡  የሆነው ነገር እንዲያስደንቀኝ ካልፈቀድኩለት እንደማያስደብረኝ ደረስኩበት፡፡

ሁላችንም በማይመች ሁኔታ ተጋፍጠናል ነገር ግን ተገቢ ያልሆነ አቋም በማስወገድ እናልፋቸዋለን፡፡ ዛሬ ይህን አስታውሱ  እግዚአብሔር ፍጹም ነውና በእርሱ መታመንን ተማሩ፡፡ እርሱ  መጥፎ ሁኔታዎችን እያሳለፈ፣ እናንተን እያበረታና ሰላምን እንድታገኙ በመምራት ያሳልፋችኋል፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንተ ፍጹም ነህ፡፡ ሰዎች እና ሁኔታዎች ሲቀያየሩብኝ  አንተ ስለማትቀያየር ደስ ይለኛል፡፡  በሚያበሳጨን ሁኔታዎች ላይ ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በአንተ ተስፋ ከማድረግ የሚመነጨውን ሰላም መርጫለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon