ከጠብ የራቀን ሕይወት መምራት

ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።ምሳሌ 17፡14

ላት በክርስቲያኖች ላይ ከሚጠቀምባቸው የጦር መሳሪያዎች አንዱ ጠብ ነው፡፡ ለጠብ አነሳሽ የሆኑ ሶስት ምክንያቶች አሉ ብዬ አምናለሁ፡-

  1. አንደበታችን፡ ጊዜውን ጠብቀን የማንናገራቸው ጤናማ ያልሆኑ ቃላቶች በእርግጠኝነት ጠብ ጠንሳሽ ናቸው፡፡ ጤናማ ያልሆኑ ቃላትን ደጋግመን በወረወርን ቁጥር እሳቱ ይፍማል፡፡ እሳቱን ለማጥፋት መደረግ ያለበትም አቀጣጣዩን ነገር ማስወገድ ነው፡፡
  2. ትዕቢተኝነት፡ ምንም እንኳን ጤናማ ያልሆኑ ቃላቶች ጠብ ቀስቃሽ ቢሆኑም እንኳን ኩሩ ልብ ግን በሰላም መቀመጥን ይጸየፋል፡፡ ኩሩነት የመጨረሻውን ቃል እኛ እንድንናገር ይፈልጋል ፣ ቃሉ ግን ይህ ድርጊት ወደ ጥፋት ይመራል ይላል። (ምሳ 16፡ 18 ይመልከቱ)
  3. ተያያችን፡ ብዙ ጊዜ የግል አስተያየታችንን ለሎች ለማሳማን በምናደርገው ጥረት ወደ ጠብ እናመራለን፡፡ ቆም ብለን ስናስበው የግል አስተያየታችንን አስፈላጊ ባልሆነበት ጊዜ መስጠታችንን ስናቆምና ምን ያህል መማር እንዳለብን ስናጤን ያኔ የሚያስፈልገንን እውቀት እንገበያለን፡፡

ጠላት ብዙ ጊዜ ሕይወታችን ውስጥ ጠብን ለማስረጽ ይሞክራል፡ ይህ ሲሆን ጠብን በመሸሽ ሰላምን ፣ አንድነትን እና ሌሎችን መረዳትን አጥብቆ በመፈልግ ለእግዚብሔር ክብር ለመስጠት መወሰን ይኖርብናል፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ወደ ጠብ እንዳልገባ አንተ ጠብቀኝ፡፡ ቃሌን እና አስተያዬቴን ላንተ እሰጥሃለሁ፡፡ ከጠብ የራቀ ግንኙነት እንዲኖረኝ እሻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon