የመፈወስ ሥጦታ

ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ሥጦታ…. ይሰጠዋል፡፡ 1 ቆሮ 12÷9

የፈውስ ሥጦታ ከእምነት ሥጣታ ጋር አብሮ ይሠራል፡፡ ምንም እንኳ ሁሉም አማኞች ሁሉ ለበሽተኞች እንዲፀልዩ የምበረታቱና እነርሱም ስፀልዩ ብሻላቸውም (ማር 16÷17-18 ተመልከት) መንፈስ ቅዱስ ግን በልዩ መንገድ የፈውስ ሥጦታን ለአንድ አንድ ሰዎች ከፋፍሎ ልክ እንደሌሎች መንፈሣዊ ሥጦታዎች ለተለያዩ ሰዎች ይህንንም ከፋፍሎ ይሰጣል፡፡ በኮንፍራንሶቻችን እኛ ሁልጊዜ ለሰዎች እንፀልይና በጣም የሚገርም የፈውስ ተዓምራቶች እናያለን፡፡ ለዓመታት እጅግ በጣም ብዙ ምስክርነቶችና ዘገባዎችን ከተረጋገጠ አካላዊ ፈውሶች ጋር እንቀበላለን፡፡ በኮንፍራንሶቻችን የእምነትን ፀሎት እፀልያለው፡፡ እንዲሁም በማስ ሚዲያዎቻችንም እንዲሁ እፀልያለሁ፡፡ እናም እግዚአብሔር በእምነት እንደሚሠራ አምናለሁ፡፡ አንድ ሰው በመንፈሳዊ ሥጦታ ፈውስን ስቀበል ያ ፈውስ ምናልባት ወዲያው ማስረጃ ላይሆን ይችላል፡፡ ፈውስ ልክ እንደመድኃኒት ሂደት ሊኖረው ይችላል፡፡ ስለዚህ በእምነት በመቀበል በሂደት እየሠራ መሆኑን ማመን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ውጤቶቹን አብዛኛውን ጊዜ በኋላ ላይ የምታዩ ናቸው፡፡ እኔ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን የማበረታታው ‹‹የእግዚአብሔር የፈውስ ኃይል አሁን በሕይወቴ እየሠራ ነው፡፡›› ደጋግመው እንዲሉ አደርጋለሁ፡፡

በእምነታችን ጉዳይ እግዚአብሔርን መታመን አለብን፡፡ ስለዶክቴሮችና ስለመድኃኒት ሳያስፈልገኝ እወስዳለሁ፡፡ ስለእነርሱም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ የእኛ መድኃኒትና ፈዋሽ ነው፡፡ (አሣ 53÷5 ተመልከት)


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እግዚአብሔር የአንተ ሀኪም ቃሉ ዳግም መድኃኒትህ ነው፡፡ በፈለገው መንገድ እንደፈውስህ ጠይቀው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon