የእዉነት መንፈስ

የእዉነት መንፈስ

ግንእርሱየእውነትመንፈስበመጣጊዜወደእውነትሁሉይመራችኋል፤የሚሰማውንሁሉይናገራ ልእንጂከራሱአይነግርምና፤የሚመጣውንምይነግራችኋል። (ዮሐንስ 16:13)

በህይወቴ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ነበሩብኝ፣ ደስተኛም አልነበርኩም፡፡ ይሁን እንጂ ለብዙ ዓመታት ራሴንና ሌሎች ሰዎችን ምክንያት አደርግ ነበር፡፡ከሰዎች ጋር የነበረኝ ግንኙነት አስቸጋሪ ነበር፣ ከማዉቃቸዉ ሰዎች ሁሉ ጋር አብሮ ለመሆን እነሱ መለወጥ አለባቸዉ ብዬ አስብ ነበር፡፡ የችግሩ መንስኤ መሆን እንደምችል በፍጹም አስቤ አላዉቅም ነበር፡፡

ከዕለታት አንድቀን በ1976 ፣ ባለቤቴ እንዲለወጥ እየጸለይኩ በነበረበት ወቅት፣ መንፈስ ቅዱስ ለልቤ ይናገረኝ ጀመር፡፡ ከኔ በስተቀር ሰዉ ሁሉ ችግር ያለበት ነዉ ብዬ ራሴን አሳምኜ ሳለሁ፣ ራሴን እያታለልኩ እንደሆነ ሲገልጥልኝ በጣም ደነገጥኩ፡፡ ለሶስት ቀናት፣ ከሱ ሃሳብ ጋር እንዳልሆንኩመንፈስ ቅዱስ ገለጠልኝ፣ ደስተኛ መሆን አለመቻል፣ ወሳኝ ሰዉ እንደሆንኩ፣ ስግብግብነት፣ የበላይመሆን፣ሁሉንም መቆጣጠርና የመሳሰሉት መንፈስ ቅዱስ ከገለጠልኝ ነገሮች መካከል ናቸዉ፡፡

እነዚህን አዉነታዎች ለመጋፈጥ ለኔ በጣም አዳጋች ሆኖብኝ ነበር፣ ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ በሰጠኝ ጸጋ፣ በብዙ ፈዉስና ነጻነት አዲስጉዞ በህይወቴ ጀመርኩ፡፡ ዛሬ የማስተምራቸዉ አብዛኛዎቹ እዉነታዎች በዚያን ጊዜ ከነበሩት ነገሮች የተነሱ ናቸዉ፡፡ ሰይጣን አታላይና የዉሸት አባት ነዉ፤ በጨለማ ዉስጥ እንድንመላለስ ካደረገ፣ በእስራትና መከራ ዉስጥ እንድንኖር ይይዘናል፡፡ እዉነትን መጋፈጥ ከባድ ቢሆንም፣ ለመለወጥና በነጻነት ለመመላለስ በጣም ወሳኝ ነገር ነዉ፡፡

ጌታ ኢየሱስ ዛሬ እንደተናገረን፣ መንፈስ ቅዱስ የእዉነት መንፈስ ነዉ፣ ይናገረናል ወደ እዉነትም ሁሉ ይመራናል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ በህይወታችን ራሳችንን የምናታልልበት ነገር ካለ መንፈስ ቅዱስ እንዲገልጥልን እንጠይቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon