ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፡፡ 1 ቆሮ 12÷8
የእውቀት ቃል በብዛት የምሠራው ከጥበብ ቃል ጋር በተመሳሳይ መንገድ ነው፡፡ ብዙ የተለያዩ የእውቀት ቃል አገላለፆች አሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የምስማሙበት እግዚአብሔር ለሆነ ግለሰብ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ያደረገውንና መልዕክቱ የምናደርሶ ወይም እውቀቱን የምናገር ግለሰብ በምንም ተፈጥሮአዊ የማወቅያ መንገድ በሌለው ወቅት የምሰራበት ፀጋ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ስነገረንና ስለሌሎች ሰዎች የዕውቀት ቃል ሲሰጠን የሆነ ነገር በሕይወታችን ትክክል እንዳልሆነ እናውቃለን ወይም የሆነ ነገር በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለማድግ ፈልገው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ መለኮታዊ ዕውቀትን በማንኛውም ሕይወት ላይ በኃይል ለማስገደድ መሞከር የለብንም፡፡ በዚህ ፈንታ በትህትና ለእርሱ የፀጋውን አገልግሎት በማቅረብ የማሳመኑን ሥራ ለእግዚአብሔር መተው አለብን፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔ ከእኛ የምፈልገው ለግለሰቦች ሙሉ በሙሉ እንድንፀልይላቸው ነው፡፡
ምንም እንኳ የእውቀት ቃል አብዛኛውን ጊዜ ለአገልግሎችን እንደ መሣሪያ ሌሎችን ለመርዳት የተሰጠን ቢሆንም ለግል ሕይወታችንም እጅግ በጣም ጠቀሜታ አለው፡፡ ለምሣሌ፡- እኔ የሆነ ነገር ሲጠፋብኝ ወይም የት እንዳኖርኩት ሥረሳ የሥጦታ በተከታታይ ሲያገለግለኝ ተለማምጃለው፡፡ የምፈልገው ነገር ሲጠፋብኝ ድንገት መንፈስ ቅዱስ በአእምሮዬ ሥዕል ያመጣልኛል ወይ ሃሣብ፣ ወይ ደግሞ የት እንዳስቀመጥኩ ቃል ይሰጠኛል፡፡ ይህ ለእኔ የተለማመድኩት ለእኔ የሚሰጠኝ የዕውቀት ቃል ገጠመኞቼ ናቸው፡፡ በተፈጥሮአዊ መንገድ የእውቀት ቃል በሕይወትህ እንዴት እንደምሰራ አላውቅም፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ትምህርት ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር እውቀት
ደግሞ የበለጠ መልካም ነው፡፡ ስለዚህ በእርሱ ላይ ለመታመን እርግጠኛ ሁን፡፡