እግዚአብሔር (አምላካችን)ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ብሩክ (ደስተኛ፣የታደለ እና ሊቀናበት የተገባ)ነው፡፡ – መዝ 34፡8
የእግዚአብሔርን ባህሪ ማወቃችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ለምን? ምክንያቱም ማስተዋልን ይሰጠናል፡፡የእግዚአብሔርን ባህሪ ካላወቅን ማን ከእግዚአብሄር እንደሆነ ማን ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ በምን እንለያለን? ከማንነቱ እና ከሚያደርገው ነገር ጋር ተስማምቼ እንድቀጥል የሚረዱኝ ሶስቱ የእግዚአብሔር ባህሪያቶች እነዚህ ናቸው፡፡
- ፍትህ፡እግዚአብሔር የፍትህ አምላክ ነው፡፡ ይህ “ፍትህ” የሚለው ቃል በጣም ምርጥ ቃል ነው ምክንያቱም ማናቸውንም የተሳሳተ ነገር ያስተካክላል ማለት ነው፡፡ይሄ ደግሞ በማይገባ መንገድ በተስተናገድሁ ጊዜ እንዳልጨነቅ ያደርገኛል ምንያቱም እግዚአብሔር ፍትህን እንደሚያደርግ አውቃለሁ፡፡ይሄ ማንነቱ ነው፡፡
- መልካምነት፡እግዚአብሔር መልካም ነው-ይሄ እውነት መቼም አይቀየርም፡፡ ነገሮች እናንተ በፈለጋችኋቸው መንገድ ሲሄዱ ወይም አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም መልካም ነው፡፡መዝ.34፡8 እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ… ይላል፡፡ነገሮች መጥፎ ሲሆኑ በእግዚአብሔር መልካምነት እጽናናለሁ፡፡
- ቅድስና፡ እግዚአብሔር ቅዱስ እና ጻድቅ ነው፣እኛንም ቅዱስ፣ንጹህ፣የጠራን እና በሀጢያት ያልረከስን ሊያረገን ይፈልጋል፡፡እውነቱን ለመናገር ወደድኩም ጠላሁ የሚያደርገው ሁሉ ልክ መሆኑን ማወቄ ከእግዚአብሔር ጋር በማደርገው ጉዞ ውስጥ በጣም ጠቅሞኛል፡፡ይሄ ከእርሱ ጋር እንድስማማ አግዞኛል፡፡
እነዚህ ሶስቱ ብቻ አይደሉም የእግዚአብሔር ባህሪያት ነገር ግን ለእኔ በጣም አስፈላጊዎቹ እና ሀይለኞቹ እነዚህ ናቸው፡፡
ለእናንተ አስፈላጊ የሆኑትን እነዚህን እና ሌሎችን የእግዚአብሔር መገለጫዎዎች እየተመለከታችሁ ጥቂት ጊዜን እንድትወስዱ አበረታታችኋለሁ፡፡ማን እንደሆነ ስታጠኑ መንፈስ ቅዱስ መገለጫዎቹ ከእናንተ ማንነት ጋር እንዲዋሀዱ ይረዳችኋል፡፡በየዕለት ተዕለት ህይወታችሁ መለማመድ ጀምሩና እግዚአብሔር የሚያደርገውን ተመልከቱ…እንዴት መልካም እንደሆነ” ቀምሳችሁ እዩ!”
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ድንቅ ነህ፤ፍትህህ፣መልካምነትህ፣ቅድስናህ እና ሌሎች የማይቆጠሩ መገለጫዎችሁ እያስደነቁ ምን ያህል ታላቅ እንደሆንክ ያሳስቡኛል፡፡የበለጠ አንተን እየመሰልኩ እንድሄድ ባህሪያቶችህን አሳስበኝ፡፡