የደስተኝነት መሠረት

የደስተኝነት መሠረት

የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ነውና እግዚአብሔርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ፡፡ መክ 12÷13

የመክብብ መጽሐፍን ቃል በቃል የፃፈው ደስታ የሚገኝበትን ነገሮች ለማግኘት የደከመ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው ብዙ ሃብት ነበረው ብርቱ ኃይል እና ብዙ ሚስቶች ነበሩት፡፡ እሱ ከማንኛውም ምድራዊ ደስታ እራሱን አልገደበም፡፡ ዓይኑ የተመኘችሁን ሁሉ ያደርግና ይወድ ነበር፡፡ እርሱ ይበላ፣ ይጠጣና ያገባም ነበር፡፡ እርሱ እጅግ ብዙ እውቀት፣ ጥበብ፣ እና ክብር ነበረው፡፡ ነገር ግን ሕይወትን ጠላ፡፡ ሁሉም ነገር ምንም ጥቅም እንደሌለው ታየው፡፡ የሕይወት ትርጉምና ምንነት ለማስላት በሞከረና በመረመረ ቁጥር ግራ እየተጋባ ሄደ፡፡

በመጨረሻ ላይ የእርሱ ችግር በምንና በምን እንደሆነ ተረዳ፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ አለመታዘዙ ነበር፡፡ እርሱ ደስተኛ ያልሆነበት ምክንያት የደስታዎች ሁሉ መሠረትና ምንጭ የሆነውን መታዘዝ እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡

ብዙ በአካባቢያችን ያሉ ግለሰቦች በብዙ ሃዘን ሰቆቃና ለቅሶ ውስጥ ሆኖ ስለ አሳዛኝ ሕይወታቸው ሰዎችንና ሁኔታዎችን እየከሰሱ ሰበብ እያደረጉና እየተራገሙ እንዲሁም የችግራቸውንና ላለመርካታቸው ምክንያትና መንስኤ ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ያለመታዘዝ መሆኑን ሳይገነዘቡ ይመላለሳሉ፡፡

ደስተኛ ለመሆን እንደምትፈልግ አምናለሁ፡፡ የደስተኛነት ቁልፍ ደግሞ እግዚአብሔርን መታዘዝ ነው፡፡ መክብብ 12÷13 የምለው ለማይመችና ላልተጣጣመ ሁኔታ ሁሉ ማስተካከያው መታዘዝ እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ማለት ማንኛውም ነገር ከትዕዛዝ ወይም ከመግባባት ውጭ ሲሆን ወደ አለመታዘዝ ሲያመጣ መታዘዝ ብቻ ወደ ስምምነትና መግባባት ይመልሳል፡፡ በሕይወታች ለውጥ የሚመጣው ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስንታዘዝ ነው፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በሁሉ ነገሮች አእምሮህን ለመታዘዝ አዘጋጅተህ ስትኖር ደስታህ እያደገ ይሄዳል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon