የጸጋዉ መንፈስ

የጸጋዉ መንፈስ

የሙሴንሕግየናቀማንኛውምሰውሁለትወይምሦስትሰዎችከመሰከሩበትያለምሕረትይገደልነበ ር።ታዲያየእግዚአብሔርንልጅየረገጠ፣የተቀደሰበትንየኪዳኑንደምእንደተራነገርየቈጠረ፣የጸጋ ዉንምመንፈስያክፋፋእንደምንያለየባሰቅጣትይገባውይመስላችኋል? (ዕብራዉያን 10:28-29 አዲሱ ትርጉም)

መንፈስ ቅዱስ የጸጋ መንፈስ ነዉ፡፡ ጸጋ አንድን ነገር ማድረግ እንድንችል ቀላል የሚያደርግልን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በመጀመርያ፣ ለእግዚአብሔር እንድንቀደስና የእሱ ማደሪያ እንድንሆን የሚረዳን ነዉ፡፡መንፈስ ቅዱስ በኛ ዉስጥ ሲሆን፣ ዉስጣችን ያለዉን የጸጋዉን መንፈስ ኃይል በራሳችን ጉልበት ማድረግ ፈልገን ያልቻልነዉን እንድናደርግ ይረዳናል፡፡

ለምሳሌ፣ በህይወቴ ዉስጥ የነበሩትን ብዙ አስቸጋሪ ባህሪያት ለመለወጥ ለብዙ ዓመታት ሞከርኩ፡፡ ጥረቴ ለዉጥ ማምጣት ባለመቻሉ ብዙ ጊዜ ተስፋ እቆርጥ ነበር፡፡ በንግግሬ ያልተገባን ነገር መናገሬን ከተገነዘብኩ፣ እንዳልደግመዉ መወሰን አለብኝ፡፡ ብዙ ነገር ባደርግም፣ ለዉጥ ማምጣት አልቻልኩም፡፡ አንዳንዴ እንዲያዉም የከፋ ነገር ዉስጥ እገባ ነበር፡፡

በመጨረሻ፣ ራሴን በራሴ መለወጥእንዳልቻልኩ ሲገባኝ፣ ድካሜን አምኜ በእግዚአብሔር ፊት አለቀስኩ፡፡ ወዲያዉኑ፣ እግዚአብሔር፣ “ መልካም፡፡ አሁን በህይወትህ አንድ ነገር ማድረግ እችላለሁ፡፡” ብሎ ለልቤ ተናገረኝ፡፡

እግዚአብሔር በህይወታችን ለዉጥ ሲያመጣ፣ እግዚአብሔር ክብር ያገኛል፤ ስለዚህ፣ እኛ ራሳችንን እንድንለዉጥ እሱ አያደርግም፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ሳንደገፍ ራሳችንን ለመለወጥ ስንሞከር፣ እሱን “ከራሳችን ነገር ዉስጥ” እያስወጣነዉ ነዉ፡፡ ራሳችንን በራሳችን ለመለወጥ ከመሞር ይልቅ፣ በቀላሉ እሱ እንዲለዉጠን መጠየቅና የጸጋዉ መንፈስ በኛ ዉስጥ እንዲሰራ
መፍቀድ ነዉ፡፡”


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ሳትጠይቅ ማንኛዉንም ነገር በራስህ ለማድረግ ፈጽሞ አትሞክር፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon