ደስተኛ ለመሆን

ደስተኛ ለመሆን

እንደተሰጠንም ደጋ ልዩ ልዩ ሥጦታ፣ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፣ ሮሜ 12÷6

እኛ ሁላችን እግዚአብሔር በሰጠን ሥጦታዎች እንድንሰራበት የተለያዩ ሥጦታና ፀጋ ለየብቻችን አሉን፡፡ የዛሬው ጥቅስ የምለው ስጦታችንን በእኛ ላይ እንዳለው ፀጋ መሠረት እንጠቀም የምልነው፡፡

ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት የማስተማር ስጦታ ልኖራቸው ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንደኛው ከሌላው በጣም ጎበዝ ልሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ያሰው ወይም ያቺ ሴት ከእግዚአብሔር ለዛ የተለየ ጥሪ የበለጠ ፀጋ ስላለው ወይም ስላላት ነው፡፡ ለምን; ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ እንደወደደ ሥጦታን ለወደደ ያካፍላልና ነው፡፡ (1 ቆሮ 12÷11 ተመልከት) እርሱ ለሚያደርገው ነገር ሁሉ የእራሱ ምክንያት አለው፡፡ በዚያ ጉዳይ እኛ ልንታመነው ያስፈልጋል፡፡ በሌሎች ሰዎች የፀጋ ሥጦታዎች የምንቀና መሆን የለብንም ይልቅስ እግዚአብሔር ለእኛ በሰጠን የፀጋ ሥጦታዎች አመስጋኞች መሆን አለብን፡፡ በአንድ ጊዜ ከሰዎች ጋር በፍቅር እየሄድን በሥጦታው ደግሞ ልንቀናባቸው አንችልም፡፡

ባለቤቴ እግዚአብሔር ለእኛ የስብከት ፀጋ በሰጠኝና ለእርሱ ደግሞ ያንን ፀጋ ስላልሰጠው ይቀናብኝ ነበር፡፡ ዴቭ ከረዥም ዓመት በፊት ያለ ፀጋውና ያለ ስጦታው ከተሰጠው ውጭ መሄድ አስደሳች እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ እርሱ እኔ የሆንኩትን ለመሆን ከሞከረ ሠላሙን ያጣል፡፡ ዴቭ የተቀባው በአስተዳደርና በፋይናንስ ጉዳይ ነው፡፡ በእኛ አገልግሎት ውስጥ የእርሱ ድርሻ የእኔው እኩል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በእርግጥ ደስተኛ ለመሆን ከፈለክ እንድትሠራው ለተጠራህለትና ለተሠጠ ፀጋ እራስህን ስጥ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ምን ማድረግና መሥራት እንዳለብህ ይናገርሃል፡፡ ደግሞም ለአንተ የተሰጠውን ፀጋ እንድትረዳ ይረዳሃል፡፡ በሌሎች ላይ አትቅና ነገር ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተመላለስ እንዲሁም በሕይወትህ ለሰው ጥሪና በአንተ ላይ ላለው ፀጋ ታማኝ ሁን፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- አንተ ልዩን እጅግ ብዙ የሆኑ ሥጦታዎችና ችሎታዎች አሉህ እናም እራስህን ከማንም ጋር ልታወዳድር አይገባህም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon