ጠበቃ አለህ

እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል; የሚያፀድቅ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሚኮንስ ማን ነው; ሮሜ 8 33

መንፈስ ቅዱስ የእኛ ጠበቃ ነው፡፡ ጠበቃ የሚለውን በጥሬ ቃሉ በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈበት የግሪክ ቃል ስንመለከት የምናገኘው፡፡ እርሱ እኛን ሊያግዘን የመጣ ረዳት፣ በእግዚአብሔር የተላከ ረዳት፣ ሊጠብቀን የተላከ መከላከያአችን እንደ ማለት ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ የመጣው በቀላሉ ስገልፅ ከእኛ ጎን በመሆን በማንኛውም መንገድ የሚያግዘን አጋዣችን ነው፡፡ መከላከል ሲያስፈልገን ይከላከለናል፡፡ ልክ እንደሕጋዊ ተከላካይ ለደንበኛው እንደሚያደርግ አስፈላጊውን መከላከል ያደርግልናል፡፡ እኛ እራሳችንን በእራሳችን በእኛ ላይ ለሚመጣው ክስ ወይም ትክክል ያልሆነ ተግባር ወይም መንስኤ መከላከል የለብንም፡፡ ለእርዳታ ከአንዱ ቅዱስ ከሆነ በመጠየቅ መልስ ለመስጠት መተማመን አለብን፡፡ ምክንያቱም እርሱ የእኛ ጠበቃ ነውና፡፡

ብዙዎቻችን ብዙ ጊዜያአቶችንንና ኃይላችንን የምናባክነው እራሳችንን በራሳችን ለመከላከል የራሳችን ስምና ዝና፣ ክብራችንን፣ ተግባራችንን፣ ቃላችንን፣ ውሳኔአችንን፣ ለመከላከል በምናደርገው ጥረት ላይ ነው፡፡ በእውነቱ ከሆነ በእንደዚህ አይነት ጊዜያአችንን እያጠፋን ነው፡፡ ሌሎች በእኛ ላይ በሚፈርዱበት ወቅት እኛ ከብዙ ጥረትና ልፋት በኋላ የልባችንን ንጽህና ለማሳመን እንሞክርና ምናልባት እናሳምንም ይሆናል፡፡ ነገር ግን የችግሩ መሠረት የእነርሱ ባሕሪ ወይም በተፈጥሮአቸው ላይ ከሆነና ዝም ብሎ ፈራጆች ከሆኑ ነው፡፡ እነርሱ ትንሽ ሳይቆዩ አሁንም ሌላ ችግር ሲመጣ ወይም ፈልገው ሲያገኙ አሁንም መልሰው እኛን ከመክሰስና ከመፋረድ አለማረፋቸው ነው፡፡ ነገር ግን ለዚህ ትክክለኛ እርምጃ የሚሆነውና እንደመፍትሔ መውሰድ ያለብን ነገር በጉዳዩ ላይ መፀለይና መንፈስ ቅዱስ የእራሱን ድርሻ በመወጣት በሕይወታችን ጥበቃና ጠበቃ እንዲሆነን መጋበዝ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚብሔር ቃል ለአንተ፡- መንፈስ ቅዱስ ለአንተ ጠበቃና ጠባቂ ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon