ጠቢብ/አስተዋይ

ጠቢብ/አስተዋይ

ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል። – ምሳሌ 16:21

ዛሬ ዛሬ በዙ የማንሰማው ቃል ቢኖር ጥንቃቄ የሚለውን ቃል ነው፡፡ ይህ ማለት ጥንቃቄ የተሞላበት አያያዝ ማለት ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ አገላለፅ ጠቢብ ማለት እግዚአብሔር እንድንጠቀምበት ለሰጠን ስጦታዎች መልካም ባለ አደራ ወይም አስተዳዳሪ መሆን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ስጦታዎች ጊዜን፣ ጉልበትን፣ አቅም፣ ጤናንና ማንኛውንም ቁሳዊ ንብረትን ያጠቃልላሉ፡፡ ሰውነታችንን፣ አእምሯችንንና መንፈሳችንንም ይጨምራል፡፡ እያንዳንዳችን የተለያዩ ስጦታዎች እንደተሰጠን ሁሉ እነዚህን ስጦታዎቻችንን የምናስተዳድርበት የተለያዩ ብቃቶችም ተሰጥቶናል፡፡

በጣም በርካታ ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ስጦታና ብቃት እርሱ እንዲጠቀሙበት ባልፈለገው መንገድ በመጠቀም ራሳቸውን ያደክማሉ፡፡ ሌሎችን ለማስደሰት ወይም የግል ዓላማዎቻችንን ለማሳካት ራሳችንን ከማድከም ይልቅ እግዚአብሔርን መስማትና የሚለንን ማድረግ ጥበብ ነው።

ሰዎችን ለማስደመምና በእነሱ ልክ ለመኖር መሞከር አስተዋይነት ወይም ጥበብ አይደለም፡፡ አስተዋይነት ማለት እግዙአብሔር የሰጠንን ስጦታ እንዴት እንድንጠቀምበት እንደሚፈልግ መጠየቅና ያንንም መታዘዝ ነው፡፡ በሕይወት እግዚአብሔር በሚፈልገው ደረጃ ደስ ለመሰኘት የእግዚአብሔርን ጥበብ ዛሬ ተምረህ በተግባር አውል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰጠኀኸኝ ነገሮች ሁሉ ላይ መልካም ባለ አደራ መሆን እፈልጋለሁ፡፡ያለኝን ስጦታና ብቃቶች ለአንተ ብቻ ለመጠቀም አሁን ወስኛለሁ፡፡ እንዴት እንደምጠቀምባቸው የአንተን ጥበብና ማስተዋል ስጠኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon