ፍቅር በድርጊት

ፍቅር በድርጊት

“እርስ በእርሳችሁ ብትዋደዱ፤ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ-መዛሙርት እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ፡፡” – ዮሀ 13፡35

ክርስቲያን እንደመሆናችን ለሌሎች ፍቅር ለማሳየት ነው የተጠራነው። ከላይ ያለው ቃል እንደሚናገረው እርስ በእርሳችን ከተዋደድን ሌሎች የኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት እንደሆንን ያውቃሉ፡፡ (ዮሀ 13፡35)

ብዙ ሰዎች ፍቅርን ልክ እንደ ስሜት ብቻ አድርገው ያዩታል፡፡ነገር ግን ከዛ በጣም የላቀ ነገር ነው፡፡እውነተኛ ፍቅር የሚታየው በድርጊታችን ነው፡፡

እነዚህ ድርጊቶች ከባድ እና አስጨናቂ መሆን የለባቸውም፡፡የኢየሱስን ፍቅር ለማሳየት አንዱ ምርጥ መንገድ ቀላል የሆነ የዕለት ተዕለት ድርጊት ነው፡፡

ትንሽዬ ስጦታ ለሆነ ሰው መስጠት ወይም ጓደኛ ከሚፈልግ አንድ ያዘነ ምስኪን ሰው ጋር ንግግር ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡

ወይም ከጎረቤት ላለችው ብቻዋን ልጆች ለምታሳድግ እና ምግብ ለማግኘት የሚከብዳት እናት አንድ ፌስታል አስቤዛ መግዛት ሊሆን ይችላል፡፡

ፍቅር ማሳየት ምናልባትም መንገድ ላይ፣አዳራሽ ውስጥ ወይም ገበያ ስፍራ የሚያልፍን ሰው ፈገግ ብሎ ሰላም የማለት ያህል ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡

የክርስቶስን ፍቅር ለመግለጽ ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ፍቅሩን ለሌላ ሰው ስታሳዩ የዛን ሰው ልብ ሊያለሰልሰው ይችላል፡፡እናም በቅጽበት ለሌሎች ለመድረስ እና ፍቅርን ለማሳየት መንገድ መፈለግ ይጀምራሉ፡፡

ስለዚህም በእግዚአብሔር ፍቅር እየተደሰታችሁ እንዲመራችሁ ፍቀዱለት፡፡በዚህ ሰዐት አንድን ሰው በልባችሁ እያስቀመጠ ይሆን?

ለኢየሱስ ያለኝ ፍቅር ለሌሎች ፍቅር በማሳይበት መንገድ እንዲገለጥ እፈልጋለሁ፡፡አንዳንድ ለመውደድ ከባድ የሆኑትን ሰዎች ጨምሮ፡፡በእግዚአብሔር ፍቅር አንድ ጠንካራ ልብ ማለስለስ ከቻልኩ ምናልባት ያ ሰው የአንድ ሌላ ሰውን ልብ በፍቅር ማለስለስ ይችል ይሆናል፡፡ይሄኛውም ሰው ደግሞ ሌሎችን ይደርሳል እናም የእግዚአብሔር ፍቅር አየቀጠለ ይሄዳል …በቅርቡ የፍቅር አቢዮት እናያለን ማለት ነው!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ለአንተ ያለኝ ፍቅር ለሌሎች ፍቅር በማሳይበት መንገድ እንዲታይ እፈልጋለሁ፡፡በመንገዴ ለምታመጣው ማናቸውም እና የትኛውም ሰው ፍቅር የማሳይበትን መንገድ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon