ፍፁም መሆን እንደማንችል እግዚአብሔር ያውቃል

ፍፁም መሆን እንደማንችል እግዚአብሔር ያውቃል

አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍፁም እንደ ሆንሁ አይደለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ፡፡ – ፊሊ 3፡12

ብዙ ሰዎች ስህተት መፈፀምን በጣም ስለሚፈሩ ምንም ነገር አይሰሩም፡፡ ይልቁንስ ቁጭ ብለው ‹‹ብሳሳትስ? እግዚአብሔርን ባጣውስ?›› የሚሉ ጥያቄዎች ራሳቸውን ይጠይቃሉ፡፡

አንድ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ብሎ እንደነገረኝ ታቃላችሁ? ‹‹አንቺ ብታጪኝ እንኳን፣ እኔ ግን አገኝሻለሁ፡፡›› ነበር ያለኝ፡፡
ወዴት እንደምንሄድ ሳናውቅ ዝም ብለን ብንንከራተት፣ አጃችንን ከፍ አድርገን ‹‹ኢየሱስ፣ ግራ ገብቶኛል፤ እባክህ ናና አግኘኝ፡፡›› ማለት እንችላለን፡፡

እግዚአብሔር ፍፁም መሆን እንደማንችል ያውቃል፣ ስለዚህ ልጁን ፍፁም መስዋዕት አድርጎ ስለእኛ ልኮታል፡፡ አሁን ከፊታችን ወዳለ ፍፅምና እየተጓዝን ነው፡፡ ጳውሎስ በፊሊጵስዩስ ምዕራፍ 3 ላይ የኋላችንን እየረሳን የፊታችንን ለመያዝ እንድንዘረጋ ይነግረናል፡፡

እግዚአብሔር ወደፊት እንድንዘረጋ ዛሬ ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ ስህተት እሰራለሁ በሚል ፍርሃት ውስጥ መኖራችንን ማቆም አለብን፤ ምክንያቱም ማንኛውም ሰው ስህተት ይሰራል፣ አበቃ! እግዚአብር ስህተት እንዳንሰራ አይደለም እየጠየቀን ያለው፤ በእርሱ እንድናምን እና ወደፊት እንድንዘረጋ ነው፡፡ እየጠየቀን ያለው ለእርዳታ እንድንጠራው ነው፡፡ ጉድለታችሁን በመፍራት ውስጥ አትኑሩ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለእናንተ ባለው ፍፁም ዕቅድ ውስጥ በእምነት ኑሩ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በጉድለቴና በስህተቴ ሽባ ሆኜ መኖር አልፈልግም፡፡ ትኩረቴን በአንተ ላይ ማድረግ እንድችል እርዳኝ፡፡ አንድ ነገር አውቃለሁ፣ ወደአንተ ብጣራ፣ ወደፍፁምነት እዘረጋ ዘንድ ትረዳኛለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon