ለራስህ ስጦታ አበርክት

ለራስህ ስጦታ አበርክት

እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩሆች ሆኑ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ፡፡ ኤፌ 4÷32

ይቅር አለማለት፣ መራርነት፣ ቅሬታ ወይም ንዴት የመሳሰሉት የእግዚአብሔርን ድምፅ እንዳንሰማ ይጎትተናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔርን ቃል በጣም ግልፅ ነው፡፡

እግዚብሔር ሃጥያታችንን ይቅር እንዲለን ከፈለግን በእርሱ ላይ ከማመጽ የሌሎችን ኃጥያት ይቅር በማለት በእራሳችን ላይ መፍረድ መፍትሔ ነው፡፡

በኤፌ. 4÷30-32 ላይ ያለው ንባብ የዛሬ ጥቅሳችን እንደሚያስተምረን በስሜታችን ውስጥ መጥፎ ነገሮችን ማለት ንዴት፣ ቅሬታ፣ ጥላቻ በልባችን ስናሰላስል መንፈስ ቅዱስን እናሳዝናለን፡፡ በሕይወታችን ይቅር አለማለትን በማንኛውም ሰው ስለማንኛውም ጉዳይ ስንቋጥር ልባችንን በማደንደን ለእግዚአብሔር ምሪት ያለንን ተነሳሽነት በሕይወታችን ይከለክላል፡፡

አንድ ወቅት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ሰማሁት በይቅርታ አለመመላስና በቅም መመላለስ ከራስ መርዝ ጠጥቶ የጠላትን ሞት እንደ መጠባበቅ ነው አለ፡፡ ለምን ሕይወትህን በንዴትና በመራራነት በሆነ ሰው የእራሱን ሕይወቱን እያጣጣመ ወይም እያጣመመች ካለ/ካለች ስለ ጉዳዩም ፈፅሞ ትዝ ለማይለው በከንቱ ታሳልፋለህ፡፡ ለራስህ ውለታ ዋል፣የበደሉህን ይቅር በል በራስህ የይቅርታ ገፀ በረከት አበርክት ለልብህ ሰላም በመስጠት የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ያስችልሃል፡፡ እንዲሁም ምሪቱን እንድትከተል በሕይወትህ ይረዳሃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ለራስህ ለሌሎች ይቅርታ የማድረግን ገፀ በረከት አበርክት፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon