ለእግዚአብሔር ሕያው መሆን

ለእግዚአብሔር ሕያው መሆን

እንደዚሁም ለኀጢአት እንደ ሞታችሁ፣ ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ። (ሮሜ 6፥11)

ያልዳኑ ሰዎች በመንፈሳዊ ነገር የሞቱ ናቸው። ይህ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ ወይም ደግሞ ጥልቅ የሆነዉን የመንፈስ ቅዱስን አሰራር መረዳትና መከተል አይችሉም ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ ወይም ተምረው ባገኙት እውቀታቸው ደግሞም ተራ በሆነው እውቀት ብቻ የተወሰኑ ናቸው፤በመገለጥ የመኖርን ጥቅምና ኃይል ማጣጣምም አይችሉም። ነገር ግን ዳግመኛ ስንወለድና በመንፈስ ሕያዋን ስንሆን እግዚአብሔር ለእኛ መናገር ይችላል ደግሞም ያለ መለኮታዊ መገለጥ ማወቅ ያልቻልናቸዉን ነገሮች ያሳየናል።

ቀደም ሲል እንድወጣቸው የሚያስችለኝ ተፈጥሯዊ ዕውቀት ሳይኖረኝ የያዝኳቸው ስራዎችና የተሰጡኝ ኃላፊነቶች ነበሩ። ነገር ግን ከጌታ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረኝ፤ስለዚህ ያለ በቂ ስልጠና መስራት የማልችላቸዉን ነገሮች እንድሠራ አስችሎኛል ።

አንድን አገልግሎት እንዴት መምራት እንዳለብኝ ወይም ጉባዔን እንዴት በብቃት ማገልገል እንደምችል በፍጹም አልተማርኩም። ነገር ግን እኔንና እግዚአብሔር በጆይስ ሜየር ሚኒስትሪስ ዉስጥ ያለውን ቡድን በተለያዩ መንገዶች ለማገልገል በሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ አስታጥቆናል። እግዚአብሔር በመንፈሱ እርምጃ በእርምጃ ይመራናል። በምንወስድው በእያንዳንዱ የእምነት እርምጃ ደግሞ እኛን ማስተማርና በመቀጠል ምን ማድረግ እንዳለብን ማሳየቱን ይቀጥላል።

ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ካለህ ልትሰራው በእርሱ የተጠራህለት ነገር ታደርገው ዘንድ ያስታጥቅሃል። እርሱን ለመፈለግና ድምጹን ለመስማት ከተጋህ ከተፈጥሮ በላይ በሆነ መንገድ ይመራሃል። እግዚአብሔር በሕይወትህ ያለዉን ዓላማ እንዴት እንደምትፈጽም ያስተምርሃል። ምናልባትም እነዚህ ሲገለጡ አሁን ሰልጥነህ ከምትሰራው ስራ እጅግ የላቁ ወይም ለመገመት የሚያዳግቱ ሊሆኑ ይችላሉ።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር በሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ ያስታጥቅሃል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon