በመንፈስ [ቅዱስ] [ለመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥርና ምሪት ምላሽ እየሰጣችሁ] ኑሩ [በልምምድ] ደግሞም ተመላለሱ እላለሁ፤ ከዚያም የሥጋን [ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነውን የሰውን ተፈጥሮ] ምኞት በእርግጥ አትፈጽሙም ። (ገላቲያ 5፥16)
ሁል ጊዜ የጌታውን ድምጽ ለመስማት ዝግጁ እንዲሆን ስልጠና እንደተሰጠው ፈረስ እኛም መልካም የመሰለንን ወይም የተስማማንባቸውን ብቻ ሳይሆን ጌታን በሁሉም አቅጣጫ ለመከተል ፈቃደኞች መሆን አለብን። እግዚአብሔር እንድናደርገው የሚነግረን ነገር ሁል ጊዜ የሚያስደስተን ላይሆን ይችላል።
እግዚአብሔርን ለመከተል አንዳንድ ጊዜ ሥጋ ‘አይሆንም’ መባል እንዳለበት እና ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ እንደማይመቸው መገንዘብ አለብን ። በአንድ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየጋለብን ሳለ ጌታ በድንገት ያስቆመንና ወደ ሌላ አቅጣጫ እንድንሔድ የሚያዝባቸው ጊዜያት አሉ። የፈለግነውን ነገር ሳናገኝ በመቅረታችን ህመም ቢሰማንም ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር መንገዶች የተሻሉ እንደሆኑ እንረዳለን። ዛሬ በምናነበው የቃል ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ እና በሥጋ መካከል ስላለው ግጭት ይጽፋል ። የመንፈስን ምሪት የምንከተል ከሆነ መልካም ከሆነው ከእግዚአብሔርሀሳብ እንድንርቅ የሚያደርጉንን የሥጋን መሻቶች አናረካም ወይም አናሟላም። ይህ ቁጥር የሥጋ ምኞቶች ይጠፋሉ አይልም፤ እኛ ሁልጊዜ ከእነሱ ጋር መታገል አለብን ። ነገር ግን በመንፈስ ለመመራት ከመረጥን፣ ሥጋዊ ፍላጎቶችን አንፈጽምም፥ዲያብሎስም መንገድ አያገኝም።
የእግዚአብሔርን ምሪት ለመከተል ስንመርጥ በውስጣችን ጦርነት እየተካሔደ እንዳለ ይሰማናል። ሥጋችን እና የእግዚአብሔር መንፈስ ብዙውን ጊዜ አይስማሙም፤እናም እኛ ስጋችን እንዲመቸው የማድረግ ፈተና ዉስጥ እንገባለን። ነገር ግን ሁላችንም ለእግዚአብሔር መንፈስ መገዛትን መማር ደግሞም የሥጋ ምኞቶችን እና ፈተናዎችን ማሸነፍ አለብን። በእግዚአብሔር መንፈስ እንድትመራ እንጂ ሥጋህ እንዲመራህ ላለመፍቀድ ዛሬ ወስን ።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር የእርሱን ምርጥ ነገር ሊሰጥህ ይፈልጋል።