በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለት

.. በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን ተምሬያለሁ፣ማጣትን ዐውቀዋለሁ፡፡ – ፊሊጲ 4፡11

መጽሀፍ ቅዱስ ሁኔታዎቻችን ምንም ቢሆኑ ያለኝ ይበቃኛል እንድንል ያስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህን የምለው ስለቸገረኝ አይደለም፤ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን፣ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ፡፡

ያለኝ ይበቃኛል ማለት ባላችሁ ለመደሰት መወሰን ነው፡፡በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ ጊዜ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን የምንማረው ለረጅም ጊዜ ያለመርካት ኑሮን ከኖርን በኋላ በመጨረሻ “ጌታ ሆይ ከዚህ በኋላ እንደዚህ መኖር አልፈልግም” ካልን በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ መንገድ መሆን የለበትም፡፡

በእያንዳንዱ ቀን ያለኝ ይበቃኛል ብላችሁ መምረጥ ትችላላችሁ፡፡በህይወት ዘመናችሁ ሁሉ ልታጠራቅሙት ከምትችሉት ንብረት ይሄ ይበልጣል፡፡

ጳውሎስ አንደኛ ጢሞ.6፡6ን ሲጽፍ ይሄንን ግልጽ አድርጎታል፤ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋር ትልቅ ትርፍ ነው፡፡

እኛን እንደሚያስደስተን እርግጠኛ የሆንበት ነገር ምንድነው? በየቀኑ በጌታ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን እና ለእግዚአብሔር “ጌታ ሆይ አንተ እንዲኖረኝ የምትፈልገው ብቻ ነው እንዲኖረኝ የምፈልገው” ማለት እውነተኛ ሰላምን እና ዘላቂ ደስታን ለማግኘት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ የምፈልገው አንተ ለእኔ የምትፈልገውን ብቻ ነው፡፡ልክ እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ በሁኔታዎች ሁሉ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን መርጫለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon