«… ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል» (እያሱ 1፡7)።
እግዚአብሔር ፈጽሞ ከፍርሃት ነጻ እንድንሆን ይፈልጋል። እርሱ በምንም ሁኔታ በእስራት ውስጥ እንድንኖር አያደርግም። እርሱ በልበ ሙሉነት እንድናደርገው ከተናገርነ ነገር በፍርሃት እንድንቆም ፈጽሞ አይፈልግም። እግዚአብሔር ከፍርሃታችን ይልቅ በእርሱ ላይ አተኩረን ስንነሳ፣ ከፍርሃት ድምጽ ይልቅ የእርሱን ድምጽ ስንሰማ በእኛ ፈንታ ለመስራት ይንቀሳቀሳል። የፍርሃት ሀሳቦች ወይም ስሜቶች ሲኖሩን ጠላታችን ሰይጣን ከእግዚአብሔርና እርሱ በህይወታችን ካለው ከእርሱ ዓላማ ሊያስተጓጉለን በቀላሉ ጥረት ያደርጋል። በህይወታችን በተለያዩ ጊዜያት ፍርሃት ተሰንቶችን ያውቅ ይሆናል። ነገር ግን እግዚአብሔርን ለመታመን መምረጥ እንችላለን። ፍርሃትን ከፈለግንና ከመረጥን ግን «ፍራ» ይለናል።
ከብዙ ዓመታት በፊት ስለ «ፍርሃት» እግዚአብሔር በልቤ ላይ ተናገረኝ። ለእያሱ «አትፍራ» ብሎ ሲናገረው ፍርሃት እግዚአብሔር እንዲያደርግ ከሚፈልገው ነገር ሊያስቆመው እንደሚሞክር ሊያስጠነቅቀው ተናገረው። እግዚአብሔር ፍርሃት እንዲቆጣጠረው እንዳይፈቅድለት ለእያሱ ተናገረው። ነገር ግን ወደ ፊት ቀጥል፣ በርታ፣ በጽናት ተሞላ አለው። ፍርሃት ሲሰማን የመጀመሪያ ማድረግ የሚጠበቅብን ነገር መጸለይ ነው። እግዚአብሔር ስሜታችንም ሆነ አዕምሮአችን በፍርሃት ላይ ድል እንደሰጠን እስክናውቅ ድረስ የእግዚአብሔርን ፊት ለመፈለግ መወሰን ይጠበቅብናል። ይህንን ስናደርግ በፍርሃት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ እናተኩራለን። እርሱ እግዚአብሔር ስላደረገው፣ እያደረገ ስላለውና ወደፊትም ስለሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ አድናቆታችንን በመግለጥና ስለማንነቱ እናመልከዋለን።
በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ በህይወታችን ፍርሃት ትጋፈጠዋለህ። በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ለመበርታት፣ ለመጽናትና ወደፊት ለመራመድ ደግመህ አስታውስ። አንድ ነገር ለማድረግ ከፈራህ እንኳን ከፍርሃትህ ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ ትኩረትህን እስታድርግ ጊዜ ድረስ ወደ ፊት ቀጥል አድርግ።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ የእግዚአብሔርን ድምጽ ተከተል እንጂ የፍርሃትን ድምጽ አይደለም።