አቤቱ መንገድህን አመልክተኛ ፍለጋዬንም አስተምረኝ፡፡ መዝ፡ 25 ÷ 4
ብዙዎቻችን የምንፈልገውን ነገር ስናገኝ በጣም እንደሰታለን፡፡ ይሄ ደግሞ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚገባ ስንቀሳቀስ ሌሎች ፍላጎቶቻችን በጣም ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ለምሣሌ፡- ለምንወስነው ጉዳይ የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስመት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ምርቱና መታዘዝ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
ባለቤቴ ደቭ (ዳዊት) እና እኔ የሆነ ስዕል በገቢያ አድራሻ ውስጥ አይተን እኔ ልገዛው ፈለኩ፡፡ ደቭ አስፈላጊያችን እንዳልሆነ ስገልፅ እኔ ቅጽበታዊ ቁጣ ተሞልቼ ዝምታ ዋጠኝ፡፡ በቀላሉ ተናድጄ ዝም አልኩ፡፡ ዴቭ ‹‹እሺ ይሁን››
‹‹ጥሩ ለእኔ መልካም መልካም በእርግጥ መልካም እኔ አእምሮዬ ማሰብ እስከቻለ ድረስ በመናገር እመልሳለሁና ለመሆኑ ለምንድንነው ሁልጊዜ ማድረግ ያለብኝን ለእኔ የምትነግረኝ ለምን እኔን እምፈልገውን በራሴ እንዳደርግ ለብቻዬ አትተይልኝም; አይ አይ አይ፡፡
ለሰዓታት ሎንበጫን ጥዬ ተቀመጥኩ፡፡ ዴቭን ለማናደድ ነበር፡፡ እርሱ የተረጋጋ ሰላማዊና ቶሎ ብሎ የማይረበሽ ማንነት ያለው ነው፤፤ ከእኔ ጋር ከመጣላት ሁልጊዜ እኔን ዝም ብዬ ለፈቃዱ ለቆ መተውን ይመርጣል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቴ ገና ያልበሰልኩና ስለ ጌታ ብዙም ስላልገባኝ ባሕሪዬ ጥሩ እንዳልሆነ አላውቅም ነበር፡፡
ከዚያ ዳዊትን ገፋፍቼ ስዕሉን እንድንገዛው ሆነ፡፡ ስዕሉን ከቤቴ ውስጥ እስኪቀመጥኩ፡፡ ከዚያ መንፈስ ቅዱስ አየሽ አንቺ አላሸነፍሽም፡፡ ስዕሉን አግኝተሻል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ከስረሻል ምክንያቱም በእኔ መንገድ አላደርግሽምና አለኝ፡፡
በሕይወት መንገድ ውስጥ አሸናፊነት ነገሮችን በእግዚአብሔር መንገድ በማድረግ ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳ የምንፈልገውን ባናገኝ እንኳ ትልቅ እርካታ ድምፁን በመታዘዛችን ብቻ እናገኛለን፡፡ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ እርካታ ደግሞ ከማንኛውም ድልና ሃብት ይሻላል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ ዛሬ፡- የእግዚአብሔር መንገድ ያንተ መንገድ ሲሆን በትክክለኛ ሰላምና ደስታ መንገድ ላይ ነህ፡፡