«… ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል» (ማቴ.10፡29 –30)።
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሊናገረን ይፈልጋል። እርሱ ደረጃ በደረጃ ሊመራህና ከመከራህ (ከችግር) ሊጠብቅህ እርሱ ወዳዘጋጀልህ መልካም ነገሮች ሊመራህ ይፈልጋል።
እርሱ እጅግ ጥቃቅን ስለሆኑ የህይወትህ ጉዳዮች ላይ ይጠነቀቅልሃል። ለዛሬው በተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እርሱ በራሳችን ላይ ያሉትን የጸጉራችንን ቁጥር ጭምር ይጠብቃል።እርሱ የልብህን ፍላጎቶች ያስባል እንዲሁም ከጭንቀትና ከፍርሃት ነጻ የምትሆንበትን እውነት ሊገልጥልህ ይወዳል።
የእግዚአብሔር ዕቅድ በመዝ 139፡16 ላይ ማንበብ እንደሚቻለው «… ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ»። ከመወለድህ አስቀድሞ እንደተዘጋጀው ከእርሱ ጋር የጠበቀ ህብረት ከእርሱ በረከቶችን እንድትካፈል ነው። እግዚአብሔር ሁሉም ቀናቶቻችንን ያውቃቸዋል። ለእያንዳንዳችንም የራሱ ዕቅድ አለው። በእያንዳንዱ ቀናት ምን ማድረግ እንዳለብን ብንጠይቀውና እርሱ እንደሚመራን ብናምነው ለህይወታችን ያለውን የእርሱን ዕቅድ ስናከናውን ራሳችንን እናገኘዋለን። በምድር ላይ ሳለን ለእኛ እግዚአብሔር ያለው ዕቅድ ፈጽሞ የማይደረስበት ይመስላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ዕቅድ እርሱ ቀውስን ትርጉም ወዳለውና ወደሚጠቅመን ነገር ሊለውጥ እንደሚችል እንድናውቅ የሚያደርግ ታላቅ ሰላም ይሰጠናል። እግዚአብሔርን ለማወቅ ጊዜ ውሰድ። ምክንያቱም የእርሱ ዕቅድ ከእርሱ ጋር ባለን የጠበቀ ህብረት የሚገለጥ ስለሆነ ነው።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- አስተውል እግዚአብሔር የዲንቢጦች ጭምር የሚያጋጥምህን ማንኛውንም ነገር እርሱ በእርግጠኝነት ይቆጣጠራል።