እግዚአብሔር አዲስ መልዕክት ይናገራል

እግዚአብሔር አዲስ መልዕክት ይናገራል

«… እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ» (መዝ. 105፡4)።

ንጉስ እዮሳፍጥ ትልቅ ሠራዊት ይሁዳን ለመውጋት ተሰብስቦ እንዳለ በሰማ ጊዜ እርሱ የሚያደርገውን ያውቅ ነበር። እርሱ ህዝብ ሰብስቦ ምክር ፍለጋ አልሄደም። ነገር ግን እግዚአብሔርን መፈለግና ቀጥታ ከእርሱ መስማትን ነበር ያደረገው። ኢዮሳፍጥ ከዚህ ቀደም ከዚህ ሌላ በሌላ ውጊያ ተሳትፎ እንደነበረው ምንም ጥርጥር የለኝም። ስለዚህ ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁኔታ እንደተጠቀመው ለምንድነው ተመሳሳይ ስልት ለመጠቀም ያልቻለው? ከዚህ ቀደም በነበረው ጊዜ አንድ ነገር ምን ያህል ሥራ ሠርቷል የሚለው ችግር የለውም። እግዚአብሔር በአዲስ ቅባት ካልቀባው በስተቀር ለአሁኑ ችግር መፍትሄ ለማምጣት ምንም ላይሠራ ይችላል። እርሱ ምናልባት የቀደመውን ስልት በመቀባት መልሶ ሥራ ላይ ለማዋል ሊጠቀምበት ይችል ይሆናል። ነገር ግን እርሱ ዛሬም አዲስ ያልተነካ ምሪት ከዚህ ቀደምም ያልሰማነው አዲስ መመሪያ ሊሰጠን ይቸላል። ስለዚህ እኛ ሁልጊዜ ወደ እርሱ መመልከት ይኖርብናል እንጂ ወደ ስልቶች፣ ወደ ቀመሮች፣ ወይም ወደ ከዚህ ቀደም ወደሠራንበት መንገዶች መተኮር የለብንም።ትኩረታችን የጥንካሬአችንና የአቅርቦቶቻችን ምንጭ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔርና ወደ እግዚአብሔር ብቻ መሆን አለበት።

ኢዮሳፍጥ ከእግዚአብሔር እስካልሰማ ድረስ ምንም ነገር እንደማያደርግ ያውቃል። አምፕሊፋይድ የሚባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት የመፈለጉን ጉዳይ «ወሳኝ ፍላጎት» ብሎ ይጠራዋል።ይህን ነገር ካለዚህ እውነት በስተቀር ፈጽሞ ሊያደርገው እይችልም። ይህ ወሳኝ ጉዳይ ለእርሱ ህይወትና ለህዝቡ በህይወት መኖር መሠረታዊ ጉድ ነው።

አንተም ምናልባት ከኢዮሳፍጥ ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነገር ገጥሞህ ይሆናል። አንተም ከእግዚአብሔር ዘንድ አዲስ መልዕክት ያስፈልግሃል። ምናልባት አንተ አሁን በውሃ ውስጥ እንደሚሰጥም ሰው በመጨረሻ ሰዓት ላይ የምትገኝ ዓይነት ስሜት ሊሰማህ ይችላል። ምናልባት ለመኖር የሚያስችል መልዕክት ከእግዚአብሔር ለግልህ ለመቀበል ተስፋ ቆርጠህ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር አንተ ከእርሱ ለመስማት ከምትፈልገው በላይ እንኳን ለአንተ ለመናገር ይሻል። ለእርሱ ጊዜህንና ትኩረትህን በመስጠት ፈልገው እንጂ ተስፋ የትቆርጥ አትህን።

ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ዛሬም ከእግዚአብሔር አዲስ መልዕክት ለመስማት የተዘጋጀህ ሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon