ወንዙ መፍሰሱን ይቀጥል

ወንዙ መፍሰሱን ይቀጥል

በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል። – ዮሐ 7፡38

እንደ አማኝ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ይገኛል መኖሪያውንም በእኛ ዘንድ አድርጓል፡፡ በእኛ ውስጥ የሚኖር የህይወት ወንዝ ነው። ይህ ወንዝ በእግዚያብሔር ለእያንዳንዳችን የተሰጠን ድንቅ ስጦታ ነው፡፡ በውስጣችንም ቀናውን የሆነ ዝንባሌ በማስታጠቅና ጤናማነትን በማጎናፀፍ ይፈሳል።

ብዙ ሰዎች ግን ይህ ወንዝ እንዳይፈስ አስቁመውታል፡፡በጣም በርካታ ጊዜያት ተስፋ ይቆርጣሉ ምንም ቢሰሩ አይሳካላቸውም፡፡በጣም ለብዙ ጊዜ ቸል ስለሚሉት ታላቁ ወንዝ ወደ ጠብታ ይቀየራል፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ታውቃላችሁ? ይህ የእናንተ ህይወት ይገልፃል?

ወንዙን በወጉ እንዲፈስ እስካልፈቀዳችሁለት ድረስ ፈፅሞ ደህነኛ ልትሆኑ አትችሉም የትም ልትቀምሱት የማትችሉትን ውሃ ልትቀምሱትም አትችሉም፡፡

በህይወታችሁ ላይ ያለውን ትግል ለማቆም ዛሬውኑ ወስኑ በየቦታው በጭቃ ውስጥ መዳከር ማቆምን አሁን ወስኑ፡፡ እነዚህን ቆሻሻ ነገሮች ከህይወታችሁ እንዲያጠራ እግዚያብሔርን ለምኑት፡፡እሱም እንዴት አድርጋችሁ መክፈት እንደምትችሉ ያሳያችኋል የማያቋረጠውንም የህይወት ውሃ ምንጭ በመጠጣት እርኩ… ተደሰቱ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ፤ በህይወቴ ውስጥ የህይወት ውሃ እንዲፈስ ዛሬ ወስኛለሁ፤ ቆሻሻና ስበርባሬ የዘጋውን ቦታ አሳየኝ እንዴት አድርጌ እንዳጠራውም ምራኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon