የበለጠው ረዳቴ

የበለጠው ረዳቴ

‹‹… ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው›› (መዝ.121፡1-2)።

ሁልጊዜ ማድረግ የሚገባንን ነገሮች ለማወቅ ወደ ሌሎች ሰዎች ፍለጋ መሄድና እንዲያመላክቱን መፈለግ ከመሄድ እኛ በእምነታችን የበሰልን (ያደግን) ልንሆን ይጠበቅብናል፡፡ ይህንን ስል ከሰዎች ምክርን ፍለጋ ወደ ሰዎች መሄድ ጥበብ እንጂ ስህተት ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን በሁሉም ነገር የሰዎችን አስተያያት በብዛት መጠየቅና በዚያ መንቀሳቀስ እጅግ ከባድ ስህተትና እግዚአብሔርን እንደመሳደብ የሚያስቆጥር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ከላይ ከዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመናገር የሚቻለው፣ ዳዊት አስቀድሞ እግዚአብሔርን ፈለገ ከዚያም እግዚአብሔር የእርሱ ብቸኛ ረዳት መሆኑን አወቀ፡፡ ለእኛም ዛሬ የሚሠራው እንደዚሁ ነው እንደ ዳዊት እኛም አስቀድመን ወደ እግዚአብሔር መመልከት ይገባናል፡፡ እኛ የሚያስፈልገን እግዚአብሔርን ለምክር የ‹‹መጀመሪያ ምርጫችን›› አድርገን የመፈለግ ልምድ ማዳበር ያስፈልገናል እንጂ እርሱን እንደ መጨረሻ ረዳት ማድርግ የለብንም፡፡

እግዚአብሔር ምናልበት ሰዎች የእርሱን ሀሳብ ግልጽ እንዲያደርጉልን፣ አዲስ እይታ እንዲቀርቡልንና እርሱ አስቀድሞ የተናገረንን ነገር እንዲያረጋግጡልን ሰዎችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ስለዚህ እርሱ ወደ ሰዎች ሊመራህ ከፈለገ አስቀድመህ እርሱን መፈለግና የእርሱን ምሪት ተከተል፡፡

በዘሁልቁ 22፡22-40 እግዚአብሔር ለሰዎች ለመናገር እንኳን አህያንም ጭምር ሊጠቀም ይችላል፡፡ እርሱ በጣም ሊናገረን ከፈለገ አስፈላጊ ከሆነ እርሱ ማንኛውን ዓይነት የመናገሪያ መንገድ ሊጠቀም ይችላል፡፡ እርሱ እንዲናገርህ በእግዚአብሔር ታምነህ ከሆነ እርሱ መልዕክቱን ወደ አንተ እንዲመጣ እርሱ የራሱን መንገድ እንደሚያዘጋጅ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡

ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ የእግዚአብሔርን እርዳታ አስቀድመህ ፈልግ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon