«… ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም» (መዝ.119፡1165)።
ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ስንወስድ ለጥሞና ጊዜ የሚረዳን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በሚያጋጥሙን ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚመራን ያለውን እውነት ለብዙ ጊዜ ጽፌዋለሁ። እግዚአብሔር በሚያጋጥሙን ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚመራን በእርግጠኝነት እውነት ነው። ነገር ግን በሁኔታዎች ውስጥ ሆነን ፊቱን ስንፈልግና ድምጹን በመስማት ስንታዘዝ ሚዛናችንን መጠበቅ ይጠበቅብናል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመለየት የግድ የሚያጋጥሙን ሁኔታዎች ብቻ እንጠቀማለን ብዬ አልመክርም።
በዚህ መጽሐፍ እንደገለጥኩት ሰላምና ጥበብ ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለባቸው። እነዚህ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ዋና ዋና መንገዶች ናቸውና እኛም ፈጽሞ ቸል ልንላቸው አይገባም። የሚያጋጥሙን ሁኔታዎች እንደ ተከፈተ በር ሆነው ሊታዩ ይችላሉ። ነገር ግን በልባችን ላይ ሰላምን እስከምናገኝበት ጊዜ ድረስ በተከፈተ በር ሁሉ ውስጥ ማለፍ አይጠበቅብንም።
የሚያጋጥሙንን ሁኔታዎች ብቻ ተከትለን መጓዝ ወደ ትክክለኛው ችግር ውስጥ ሊከተን ይችላል። እግዚአብሔር አጋጣሚ ሁኔታዎችን ሊዘጋጅልን እንደሚችል ሁሉ ሰይጣንም ሊያዘጋጅልን ይችላል። ምክንያቱም ሰይጣን እኛ በምንኖርበት ተፈጥሮአዊ ዓለም ውስጥ ገብቶ ለመሥራት መንገድ ስለሚያገኝ ነው። ስለዚህ የሚያጋጥሙንን ሁኔታዎች ብቻ ተከትለን የምንጓዝ ከሆነና ከእግዚአብሔር የምንሰማውን ሌሎች መንገዶች ከግንዛቤ ውስጥ የማናስገባ ከሆነ በመታለል ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን።
ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ተቃራኒ ጉዞ መጓዝ እንደማንችል እናውቃለን። እኛ በሰላም መመራትና ጥበብ በመመላለስ ይገባናል። የሚያጋጥሙን ሁኔታዎች እንዲመሩን ከመፍቀዳችን በፊት በልባችን ውስጥ የሚፈሰውን የሰላም ደረጃ /መጠን/ «በውስጣዊ ማረጋገጫ» በመፈተን በቀላሉ ልናረጋግጥ እንችላለን። ከእግዚአብሔር ለመስማት በጣም አስተማማኝ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመሆን መንገዶችን በማቀናጀት ነው። እናም እነዚህ መንገዶች በህይወታችን እንዲረዱን ነገሮችን በመፈተን የማረጋገጥ ዘዴ ሚዛናችንን ለመጠበቅ መፍቀድ አለብን። የእግዚአብሔር ቃል ምክር ሁሉ ላይ በመመሥረት ሁልጊዜ ከሁሉም የበለጠውን መንገድ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን እንጂ እኛ ከምንፈልጋቸው ነገሮች ጋር የሚስማሙትን የተወሰኑ ክፍሎች ብቻ መርጠን ለመውሰድ መሞከር ሞኝነት ነውና ፈጽሞ እናዳታደርገው።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ሁልጊዜ ውሳኔ ለመወሰን ስትል በልብህ ላይ ያለውን ሰላም ተከተል።