ለእግዚአብሔር ቅባት ቁልፉ ነገር

ለእግዚአብሔር ቅባት ቁልፉ ነገር

«… አንተም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ይህ ለልጅ ልጃችሁ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሁንልኝ። በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱም የተሰራ ሌላ ቅብዓት አታድርጉ፤ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን» (ዘጸ. 30፡31-32)።

በህይወቴ ከእግዚአብሔር ቅባት (ከህልውናውና ኃይሉ) በስተቀር የማቀርበው ምንም ነገር የለም። እኔ ሰውን የሚማርክ ቁመና ያለሁ አይደለሁም፤ እኔ አልዘምርም ወይም ሌሎች ነገሮችን አላደርግምሰዎች እንዲነቃቁ ለማድረግ እኔ የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ አቀርባለሁ። ሰዎች የድል ህይወት እንዲኖራቸውና በተግባራዊ መንገድ ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንዲችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳቶችን አቀርባለሁ። ሰዎች እንዴት በህይወታቸው ተለውጠው ይበልጥ ደስተኛ ለመሆን እንዲችሉና እንዴት በመንፈሳዊ ህይወታቸው እንደሚያድጉ እናገራለሁ። በየቀኑ ህይወታቸው የእግዚአብሔር ቃል እንዴት እንደሚረዳቸው አስተምራለሁ። በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ደርሷል። ነገር ግን እርሱ ለጠራኝ አገልግሎት የሚያስፈልገኝ የእግዚአብሔር ቅባት የግድ ያስፈልገኛል። አለበለዚያ እኔ በማንም ምንም ሥፍራ የሌለኝ እሆናለሁ። በፍቅር ካልተመላለስኩ የእግዚአብሔርን ቅባት እንደማልሸከም ተምሬአለሁ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሥጋዊ አስተሳሰብ (የራሳችን ሥጋዊ ምኞትና ሥጋዊ አመለካከት ወይም ባህሪይ) አይቀባም።

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በብሉይ ኪዳን ካህናት ላይ የቅባት ዘይት ሲፈስስ እናነባለን። ቅባቱ በምንም ሁኔታ በሥጋ ላይ መፍሰስ አይገባም፤ አይችልም። እግዚአብሔር ሥጋዊ ባህርይን አይቀባም። እኛ በእውነት በፍቅር መመላለስ አለብን። ምክንያቱም በህይወታችን ቅባቱ እንዲጨምርና እንዲረዳን ነው። ይህ ቅባት እግዚአብሔር ለጠራን ሥራ ብቁ እንድንሆን ኃይልን ይሰጠናል። የእግዚአብሔር ቅባት የእርሱ ህልውናና የእርሱ ኃይል ነውና በራሳችን አቅም ታግለን ምንም ፈጽሞ መፈጸም የማንችለውን በቀላሉ መፈጸም (ማከናወን) እንድንችል ብቃትን ይሰጠናል (ያስችለኛል)። ሁላችንም የእግዚአብሔር ቅባት ያስፈልገናል። አንድ ሰው መንፈሳዊ ሥራ ተብሎ የሚጠራውን ለመሥራት ከሌላው በላይ የእግዚአብሔር ቅባት ያስፈልገዋል። መልካም ወላጆች እንድንሆን፣ የተሳካ ትዳር እንዲኖረን፣ መልካም ወዳጅ ለመሆንና በምናደርገው ማንኛውም ነገር ሁሉ ውስጥ የእግዚአብሔር ቅባት ያስፈልገናል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ የእግዚአብሔር ህልውናና ኃይል የሆነው የእግዚአብሔር ቅባት በማንኛውም ነገር ሁሉ ውስጥ ስኬታማ እንድንሆን የሚያስፈልገን ነገር ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon